መንግሥት በትግራይ ክልል ረሃብ አለ መባሉን አጣጣለ

በትግራይ ክልል ረሃብ እንደሌለ የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ተናገሩ። ረቡዕ ዕለት በትግራይ የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ያከናወናቸውን የተግባራት በተመለከተ ከጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ጋር ለጋዜጠኞች በተሰጠ ማብራሪያ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ከአጋሮቹ ጋር በመተባበር የሰብዓዊ ድጋፍ እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።…