በትግራይ ክልል ርሃብ ሊከሰት ይችላል የሚለውን የዐለማቀፍ የሰብዓዊ ዕርዳታ ተቋማት ስጋት መንግሥት አጣጥሎታል።

በትግራይ ክልል ርሃብ ሊከሰት ይችላል የሚለውን የዐለማቀፍ የሰብዓዊ ዕርዳታ ተቋማት ስጋት መንግሥት በጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት በሰጠው መግለጫ አጣጥሎታል። የብሄራዊ አደጋ መከላከያ እና አስተዳደር ኮሚሽን ሃላፊው ምትኩ ካሳ፣ የምግብ ዕርዳታ ዕጥረት በሌለበት ሁኔታ የርሃብ ስጋት ሊኖር አይችልም ሲሉ በመግለጫው ላይ ተናግረዋል። ርሃብ ተከስቷል ለማለት የሚያስችሉ መስፈርቶች እንዳልተሟሉ እና በክልሉ ለተረጅዎች የሚከፋፈል የምግብ ዕጥረት እንደሌለ የገለጹት ሃላፊው፣ የሕወሃት ታጣቂዎች ግን በዕርዳታ ጫኝ ካሚዮኖች ላይ ጥቃት በመሰንዘር የዕርዳታ ማከፋፈሉን ሥራ አዳጋች አድርገውታል ብለዋል።