በእያንዳንዱ ደቂቃ ስጋት አለብኝ – እስክንድር ነጋ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


” በእያንዳንዱ ደቂቃ ስጋት አለብኝ” ሲል እስክንድር ነግሮኛል አሉ የባልደራስ ፓርቲ ቢሮ ሀላፊ አቶ ገለታው ዘለቀ

አቶ ገለታው ዘለቀ ለኢትዩ ኤፍ ኤም እንዳሉት በትላንትናው እለት ሄጄ አመራሮቹን ሳናግርም ተገቢው ምላሽ አልሰጡኝ ብለዋል፡፡

የባልደራስ ለእውነተኛና ለዴሞክራሲ ፕሬዝደንት እስክንድር ነጋ ከሰሞኑን ከነበረበት ማረሚያ ክፍል ትንኮሳዎችና የቃል ስድቦች ስላሉብኝ በማለቱ ክፍል ተቀይሮለት እንደነበር አቶ ገለታው ነግውናል ፡፡

ሆኖም የቅየራው ክፍልም ለስነልቦናው የማይመጥንና አደጋ ያንዣበበበት ስለመሆኑ ጨምረው ያስረዳሉ ፡፡

አቶ ገለታው አክለውም በትላንትናው እለት ወደማረሚያ ቤት ሄጄ ነበር “በእያንዳንዱ ደቂቃ ስጋት አለብኝ” ሲል እስክንድር ነግሮኛል ብለውናል፡፡

ሌላኛዋ የባልደራስ ፓርቲ አመራር አስቴር ስዩም(ቀለብ) የደህንነት ስጋት አለብኝ ይሄንንም ለማረሚያ ቤቱ ባሳውቅም ምላሽ ላገኝ አልቻልኩም እንዳለች ገልጸዋል፡፡

የፓርቲው የቢሮ ሀላፊ አቶ ገለታው የእስክንድር ነጋ ጉዳይ ከማረሚያ ቤቱ ውጪ ያለ እጩነቱን ከማይፈልጉ ሀይሎች የፖለቲካ እጅ አለበት ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እስክንድር ነጋ በአሁኑ ሰአት ታራሚ ብቻ ሳይሆን እጩ ተወዳዳሪ እንደመሆኑ ስጋት ወደማይገባው ቦታ ማዘዋወር የማረሚያ ቤቱ ሀላፊነት ነው ይህንንም እየጠየቅን ነው ሲሉ አቶ ገለታው ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

ኢትዩ ኤፍ ኤም