የመጨረሻዎቹ የዴሞክራሲ ገንቢ እና ጠባቂዎች ራሳችን ኢትዮጵያውያን እንጂ ወዳጆቻችን አይደሉም – ጠ/ሚ አብይ አሕመድ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የምርጫ ቅድመ ዝግጅት ግምገማን ከክልል ፕሬዚደንቶች እና ከምርጫ ቦርድ ጋር በሳምንታዊነት ማካሄዳችንን ቀጥለናል።

የመራጮች ምዝገባ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ነው። እስካሁን ያልተመዘገባችሁ ዜጎች በተራዘመው የምዝገባ ጊዜ ተጠቅማችሁ የምርጫ ካርድ እንድትወስዱ አበረታታለሁ። በምርጫ ጣቢያዎች የጸጥታ አካላት ምደባ እየተካሄደ ሲሆን፣ በቀጣይ ሳምንታት የሚሰማሩ ይሆናል።

የመጨረሻዎቹ የዴሞክራሲ ገንቢ እና ጠባቂዎች ራሳችን ኢትዮጵያውያን እንጂ ወዳጆቻችን አይደሉም። ባለቤት ይወስናል፤ ወዳጅ ደግሞ ያግዛል። የምርጫው ሂደት ስኬታማ እና ሰላማዊ እንዲሆን በጋራ እንሥራ። – ጠ/ሚ አብይ አሕመድ