አቶ አበረ አዳሙ ዛሬ ጠዋት የህመም ስሜት ተሰማኝ ብለው ወደ ሆስፒታል ከሄዱ በኋላ ህይወታቸው አለፈ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


May be an image of 1 person

ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ዛሬ ጠዋት የህመም ስሜት ተሰማኝ ብለው ወደ ሆስፒታል ከሄዱ በኋላ ማረፋቸው ታውቋል።
ከሳምንት በፊት ከአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነርነት የተነሱት አበረ አዳሙ፣ በድንገተኛ ህክምና ላይ እንዳሉ በልብ ህመም ችግር ህይወታቸው ማለፉን የሆስፒታል ምንጮች ገልፀዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

የቀድሞ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽነር መሞታቸው ቢረጋገጥም ፤ አቶ አበረ አዳሙ ባለፈው ሳምንት ከአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነርነት ስልጣናቸው ተነስተው በሌላ የተተኩት አበረ አዳሙ ዛሬ መሞታቸው ነው የተነገረው።

የመንግስት የማሕበራዊ ሚዲያ አንቂዎች አቶ አበረ አዳሙ በልብ ሕመም እንደሞቱ እየተናገሩ ነው። መንግስትን የሚቃወሙ አካላት አቶ አበረ የሞቱት በሴራ ፖለቲካ ተጠልፈው ነው ተገለዋል ይላል። የአሟሟታቸውን እውነተኝነት ከገለልተኛ አካል ማረጋገጥ አልተቻለም።

– አቶ አበረ አዳሙ በድንገተኛ ህመም ህይወታቸው ማለፉን የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታውቋል።

– አንድ የሆስፒታሉ ሐኪም እንደተናገሩት አቶ አበረ አዳሙ ሕይወታቸው ያለፈው በህክምና ላይ እያሉ ነበር። ሐኪሙ ከድንገተኛ ሕመሙም ሆነ ከክስተቱ ጋር የተያያዙ ተግባራትን እያከናወኑ በመሆኑ ለጊዜው ዝርዝር መረጃ ለመስጠት አልፈለጉም፡፡

– የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር መሰረት ደባልቄ “ኮሚሽነር አበረ ዛሬ ጠዋት ልቤን አመመኝ ብሎ ወደ ሆስፒታል እንደሄዱና በህክምና ላይ እንዳሉ ህይወታቸው አልፏል” ብለዋል፡፡

– የኮሚሽነር አበረ አዳሙ አስክሬን ለተጨማሪ ምርመራ ወደ አዲስ አበባ ተልኳል::