ሲጠሩት አቤት ሲልኩት ወዴት የሚል የሕወሓት አይነት አገዛዝ አንፈልግም !


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ሲጠሩት አቤት ሲልኩት ወዴት የሚል የሕወሓት አይነት አገዛዝ አንፈልግም !

የአውሮፓ ሕብረትና አሜሪካ ተላላኪ መንግስት በኢትዮጵያ ለማስቀመጥ የሚያደርጉት ሙከራ የቀጠለ ሲሉ ሲጠሩት አቤት ሲልኩት ወዴት የሚል የሕወሓት አይነት አገዛዝን በኢትዮጵያ ለማገንባት እየታገሉን ነው። የውጪ ኃይሎችን ጫናና ግፊት ተቋቁመን የምናሸንፈው ለሐገራችን ሕልውና ስንል ነው። ምርጫውና የሕዳሴው ግድብ የጎን ሕመም የሆነባቸው ምክንያት ከብሔራዊ ጥቅማቸው አኳያ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል።

በኢትዮጵያ የውስጥ ቀውስ እንደበረታ የማይካድ ሀቅ ቢሆንም የውስጥ ቀውሳችንን ተከትለው ሐገራችንን ከጉዞዋና ከ አንድነቷ ለማደናቀፍ ደፋ ቀና የሚሉ የውጪ ኃይሎች ሳይተኙ ማደራቸውን የምንመለከተው ከሚያወጡት መግለጫና ከሚያደርጉት ጉዞ መሆኑን መረዳቱ ቀላል ነው። በተደጋጋሚ በታሪካችን ውስጥ እንዳየናቸውና ያደረጉትን እኩይ ተግባር እንደምናውቀው ምእራባውያን ለብሔራዊ ጥቅማቸው እንጂ ለእኛ የሚፈይዱል አንድም ነገር የለም።

የአውሮፓ ሕብረት እኮ የምርጫ ቦርድን የስራ ኃላፊነት ወስጄ መስራት አለብኝ ብሎ ጝም ስላለ ተሽቀዳድሞ ታዛቢ አልክም የሚል መግለጫ ሰጠ እንጂ ቀድሞውም ታዛቢ የጠየቀው ለምርጫው ድጋፍ ስጠን ብሎ የለመነው የለም። ይ
አ አሜሪካንም መንግስት ቢሆን ለሐገራችን የሚያስብላት ለምስራቅ አፍሪካም የሚሳሳለት ለማስመሰል አዲስ ዲፓርትመንት አቋቁሞ አዲስ ተሿሚ በመላክ መጨቃጨቅን መርጧል።

አብዛኛው ታዳጊ ሐገራት በዲምክራሲና በእድገት እንዳይጎለብቱ ኃያላን ነን የሚሉ ሐገራት ከፍተኛ ጫና በመፍጠር የሐስት ክስ በመደርደር በሰብዓዊ መብት ዙሪያ በመሽከርከር መንግስት እስከመለወጥ የሚያደርሱ ቅጥረኞችን በመፈልፈል የሐገራትን ሰላምና ፀጥታ በማደፍረስ ግንባር ቀደም ሚናቸውን እየተወጡ ነው።

እነዚህ ኃያላን ለራሳቸው በሚያመች መልኩ ካልሆነ በስተቀር ለሕዝብ የሚያስብ መንግስት እንዲገነባ አይፈልጉም። ከሕዝብ ሰላምና ደሕንነት በፊት ብሔራዊ ጥቅማቸውን ይፈልጋሉ። ለዚህ ደግሞ መፍትሔው ለውጪ ኃይሎች ረብ የለሽ ድለላ ባለመንበርከክ በ አንድነት በመቆም የውጪ ኃይሎችን ማሳፈር ያስፈጋል። መንግስትም ለውጪ ኃይሎች መንደርደሪያ የመግለጫ ጋጋታ ምክንያት የሆኑ የውስጥ ቀውሶችን በፍጥነት መፍታትና ማስተካከል ይጠበቅበታል። #MinilikSalsawi