አዲስ አበባ ላይ ሁለቱም ከንቲባዎች በምን መልኩ ነው የተመረጡት ? ህገመንግስቱን የጣሰ ስራ ነው የተሰራው


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


<እነ ኬንያና ጋና በእምነትና በዘር ላይ የተመሰረተ ፓርቲ አይፈቅዱም። እንዴት ከሩዋንዳ አንማርም። ሩዋንዳውያን እኮ አንድ ሚሊየን ህዝባቸውን ቀብረው ነው ከስህተታቸው የተማሩት። እንዴት እኛ እስካሁን ከሞተብን ህዝብ አንማርም። ኢትዮጵያ ውስጥ አስክሬን እንኳን ክብር ነበረው። በዶዘር እስከመቅበር ደረስን እኮ።>> አቶ አበበ አካሉ/ የኢዜማ እጩ ተወዳዳሪ

<<አንድ ከተማ ላይ ከንቲባ የሚሾመው በገዢው ፓርቲ ነው። የምክር ቤት አባል ከንቲባነት ተሹሞ ያውቃል? ህግ መጣሱን ህወሃት ነች የጀመረችው። ዶክተር ደብረፂዮን ከፓርላማ ተነስተው የክልል ፕሬዝዳንት ሲሆኑ ህግ ተጥሶ ነው። ከሳቸው ተጀመረ። ከዛ በአዲስ አበባ ከንቲባ ቀጠለ። በኦሮምያና በአማራ ክልል ቀጠለ። አዲስ አበባ ላይ ሁለቱም ከንቲባዎች በምን መልኩ ነው የተመረጡት። የአዲስ አበባ ምክር ቤት ስምንት አመት ቁጭ ብሎ ተጎልቶ ከሌላ ቦታ መጥቶ ነው የተሾመላቸው። ምክር ቤቱ ለምን ተቋቋመ። ህዝቡ እኮ የዛሬ ስምንት አመት ድምፁን የሰጠው እዛ ምክር ቤት ውስጥ ላሉ አባላት ነው። ከነኛ ውጪ ለምንድነው መሾም ያስፈለገው። ደካማ ቢሆኑም ከዛው ወስደን ነው ማስቀመጥ ያለብን። ያዲሳባ ነዋሪ የመረጠው ሰው እዛ መቀመጥ አለበት። ከሌላ ቦታ አምጥተህ የምትሾምለት ለምንድነው። እቁብና እድር ላይ ዳኛ በግድ ይሾማል እንዴ። ይሄ ባህላችን እየጠፋ ነው የመጣው። ባጠቃላይ ህገመንግስቱን የጣሰ ስራ ነው የተሰራው።>>

<<ከክልል አንፃር የሲዳማ ጥያቄ መልስ አገኘ ብለን እልል አንልም። ከሲዳማ በኋላ ወላይታና ሌሎች አስር የሚጠጉ የደቡብ አካባቢ ህዝቦች ጥያቄ አነሱ። እነከንባታ እነጠንባሮ ጥያቄ አነሱ። ይሄን ጥያቄያቸውን ግን ማስተናገድ አልቻለም ይሄ መንግስት። በብሄርና በቋንቋ ላይ ከተመሰረተ ፌደራሊዝሙ ለምንድነው ደቡብ ላይ ለታጨቁት ሃምሳምናምን ብሄሮች የክልልነት እድሉን የማይሰጣቸው። የኢትዮጵያ ህዝብ በግጦሽ የሚጋጭ ነው። እዛው ባለው ማህበረሰብ በሽምግልና ይፈታዋል። አሁን ግን የወሰን ጥያቄ ሆነ። ይሄ ያንተ ክልል ነው ስትለው ግዛቱን አስፍቶ ይሄድና ጦርነት ውስጥ ይገባል። ኢዜማ ብሄርን ቋንቋና ባህልን ባሰባጠረ መልኩ የህዝብን ይሁንታ ጨምሮ የተሻለ ፌደራሊዝም ይኖረናል ነው የሚለው።>>

<<ኢዜማ ከሃገር በላይ ስልጣን አይፈልግም። ኢትዮጵያ የአይናችን ብሌን ናት። ሃገር ስትኖር ነው ስልጣን የሚኖረን። በታሪኳ ኢትዮጵያ ምርጫ አድርጋ አታውቅም። በምርጫ የሚወጣና የሚወርድ መንግስት መኖር አለበት። ቋንጣና ስልጣን ተሰቅሎ አይቀርም። ቋንጣውን ዘልዝሎ የሰቀለው አውርዶ ይበላዋል። ስልጣን ላይ ያወጣው ህዝብም በካርዱ ያወርደዋል። የጦርነት ታሪካችን ማብቃት አለበት።>>

<<ቋንቋ ሊያባላን አይገባም። እኔ ሶስት ቋንቋ እናገራለው። ኦሮሚኛና ሲዳሚኛ እናገራለው። ያደግኩት እዛ ማህበረሰብ ውስጥ ነው። ወንዝ ነው የሚያሻግረኝ። ከሰው ጋር ነው የሚያግባባኝ። ብልፅግና በማኒፌስቶው ያንኑ ፌደራሊዝም እናስቀጥላለን ነው የሚለው። ከነችግሩ። እንዴት ሰው ከህወሃት ውድቀት አይማርም። ቄሮ ለምን ታገለ፣ ዘርማ ለምን ታገለ። ፋኖ ለምን ታገለ። ለምን የኢትዮጵያ ህዝብ ታገለ። ለምን ሰዎች እስር ቤት ገቡ። ለምን ተገደሉ። ያንኑ ስርአት ለማስቀጠል? ማልያ መቀየር ነው እንዴ ለውጡ። እሱማ እባብም ቆዳውን ይቀይራል እኮ። መርዙ ግን ምላሱ ላይ እንዳለ ነው።>>

<<በክብር ወርዶ የተቀመጠ ኢትዮጵያዊ መሪ አይተናል? አንድም እኮ የለም። እርስ በርስ ከሚያገዳድለን ፖለቲካ ነፃ እንውጣ። አብረን እንኑር።