ከምርጫዉ በፊት ድርድርና ዉይይት ወይስ ከድርድርና ዉይይት በፊት ምርጫ ይቅደም ?


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


DW Amharic : ጤና ይስጥልኝ እንደም ዋላችሁ።ዓላማቸዉን በጠመንጃ ዉጊያና ጥቃት ከግብ ለማድረስ ከሸመቁት ኃይላት ዉጪ ያሉት፣ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች፣ የፖለቲካ ተንታኞችና አቀንቃኞች እሶስት ምናልባትም አራት ተከፍለዉ በየፊናቸዉ ብዙ ጊዜ ለዉይይት፣ ንግግር ክርክር የሚሆኑ፣ አልፎ አልፎ ፍፁም የሚቃረኑ የሚመስሉ አስተያየት እየሰጡ፣ ዕቅድ ዝግጅትም እያደረጉ ነዉ።

የመጀመሪያዎቹ፣ ገዢዉ ፓርቲ ከመንግስት ቢሮ ክራሲ ጋር የሚካተቱበት በመጪዉ ግንቦት ማብቂያ አጠቃላይ ምርጫ ለማድረግና በምርጫዉ ለመሳተፍ የተዘጋጁት ናቸዉ።

ሁለተኞቹ፣ መንግሥትና ገዢዉ ፓርቲ ያደርስብናል ያሉት ተፅዕኖ ካልተቃለለ ወይም ካልቆመ በምርጫዉ መሳተፍ አንችልም ብለዉ እራሳቸዉን ያገለሉት ናቸዉ።የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)ና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከነዚሕ ተርታ የሚጠቀሱ ናቸዉ።በተለይ ኦፌኮ ከምርጫዉ በፊት ድርድርና ዉይይት ይቅደም የሚል አቋም ይዟል።

ሶስተኞቹ፣ በአብዛኛዉ የፖለቲካ አንቃኞችን (አክቲቪስቶችን) እና ተንታኞችን ያካተተ ሲሆን ሐገሪቱ በጦርነት፣ በጎሳ ላይ ባነጣጠረ ጥቃትና ግጭት ዉስጥ እያለች፣ በብዙ መቶ ሺሕ ምናልባት በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ተፈናቅሎ ምርጫ ማድረግ አይቻልም ባዮች ናቸዉ።ከነዚሕ ወገኖች አብዛኞቹ ኢትዮጵያን ለገጠመዉ ችግር መፍትሔዉ ሁሉንም ወገኖች ያሳተፈ የፖለቲካ ዉይይት፣ ከተቻለም ብሔራዊ ያንድነት መንግሥት መመስረት እንጂ ምርጫ በዚሕ ወቅት ጥሩ አማራጭ አይደለም የሚሉት ናቸዉ።

ምናልባት አራተኛ የሚባሉት «ቆይተን የሚሆነዉን እንይ» ዓይነት የሚሉት ናቸዉ።እነዚሕ ወገኖች ምርጫዉን የሚያዩት ሌላ አማራጭ እንደጠፋበት አማራጭ ነዉ።ምርጫዉ ሌላ አማራጭ ያልተበጀለትን የሐገሪቱን ችግር ለማቃለል ከጠቀመ እንሳተፋለን፣ ነገር ግን በፀጥታ መታወክ ምክንያት በቂ ዝግጅትና ቅስቀሳ የታጎለበት፣ ነፃ፣ ፍትሐዊነቱም የሚያጠራጥር ነዉ ባዮች ናቸዉ።ሕብር ኢትዮጵያ ከነዚሕ ጎራ ይቦደናል።

እስካሁን እንደታዘብነዉ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ተቀራርበዉ ለመነጋገር እና የጋራ አቋም ለመያዝ የሚያደርጉት ጥረት ብዙም ለፍሬ የበቃ አይመስልም።እንዴት ይቀጥላሉ? የሚሻለዉ አማራጭስ የትኛዉ ይሆን? የዛሬዉ ዉይይታችን ትኩረት ነዉ።

በምርጫዉ ለመሳተፍ ከወሰኑት የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የገዢዉ ፓርቲ ባለስልጣናትን ለመጋበዝ ደጋግመዉን ደዉለን ነበር።አይመልሱም።የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የተባለዉ ፓርቲ ባለስልጣናትን በዉይይቱ ለመሳተፍ ቃል ገብተዉ፣ ቀጠሮ ይዘን ነበር።ነገር ግን ዛሬ ቀትር ላይ ደዉለዉ «በምርጫዉ ከማይሳተፉት ጋር» አንወያይም ብለዉናል።

ሶስት እንግዶች ግን አሉን።

አቶ ጥሩነሕ ገምታ———የኦሮሞ ፌደራዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) የፅሕፈት ቤት ኃላፊ

አቶ ግርማ በቀለ—–የሕብር ኢትዮጵያ ለዴሞክራሲ ፓርቲ (ሕብር) ሊቀመንበር

ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ—————- የሕግ እና የፌደራላዊ ሥርዓት አዋቂ ናቸዉ።

ነጋሽ መሐመድ