የኢትዮጵያ ምርጫ አሁን ባለበት ሁኔታ ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን አያሟላም


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አምስት የአሜሪካ ሴናተሮች ኢትዮጵያ ከአምስት ሳምንታት በኋላ የምታካሂደው ምርጫ አሁን ባለበት ሁኔታ ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን አያሟላም አሉ።

ሴናተሮቹ ይህን ያሉት በቅርቡ የፕሬዝደንት ጆ ባይደን አስተዳደር የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ለተሾሙት አምባሳደር ጆፍሪ ፌልትማን በጻፉት ደብዳቤ ነው። ሴናተሮቹ ቤንጃሚን ኤል ካርዲን፣ ቲም ኬይን፣ ጃኪ ሮስን፣ ኮርይ ኤ ቡከር እና ኤድዋርድ ጄ ማርኬይ ስለመጪው አገራዊ ምርጫ፣ ስለትግራይ እና በሌሎች የአገሪቱ ስፍራዎች ስላሉ ግጭቶች ለተሿሚው ልዩ መልዕክተኛ መልዕከታቸውን አጋርተዋል።

“ምርጫው ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን አያሟላም”

ሴናተሮቹ ከሳምንታት በኋላ የሚካሄደው አገራዊ ምርጫ አሁን ባለበት ሁኔታ ነጻ፣ ሚዛናዊ እና ግልጽ ሆኖ ዓለም አቀፍ መመዘኛዎች አያሟላም ብለዋል።

በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው ተዓማኒነት ባለው መልኩ ሊካሄድ አይችልም በሚል ምክንያት ራሳቸውን ከምርጫው ማግለላቸውን ሴናተሮቹ በደብዳቤያቸው አስታውሰዋል።

በሺህዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ ፓርቲ ደጋፊዎች እና አመራሮች መታሰር በምርጫው እምነት ለማጣታቸው አንዱ ምክንያት መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሴናተሮቹ ምርጫውን በተመለከተ ይህን ማለታቸውን ተከትሎ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስተያየትን ለማካተት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር እና ኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲዎች አባላቶቻችን እና አመራሮችን ለእስር እየተዳረጉ ነው፣ ቢሮዎቻችን እየተዘጉ ስለሆነ በምርጫ ለመሳተፍ የሚያስችል ሁኔታ የለምበሚል ምክንያት በምርጫው እንደማይሳተፉ ማስታወቃቸው ይታወሳል።

ይሁን እንጂ ከዚህ ቀደም ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ይሁን መንግሥት ቀጣዩ ምርጫ ዲሞክራሲያዊ እና ተዓማኒነት ያለው ለማድረግ እየሰሩ መሆኑን በተደጋጋሚ ገልጸዋል።

ሴናተሮቹ፤ “የኢትዮጵያን ሕዝብ እምነት ለማግኘት አስፈላጊ የሆኑ ማሻሽያዎች ሳይደረጉ ምርጫው የሚካሄድ ከሆነ ዘርን እና ፖለቲካን መሠረት ያደረገው ውጥረት በመላው አገሪቱ ነግሶ ወደ ከፋ ግጭት ሊያመራ ይችላል የሚል ስጋት አለን” ብለዋል።

BBC