ለአብይ አህመድ እጅ የሰጡ “የምሁር” ባንዶች ጫጫታ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ለአብይ አህመድ እጅ የሰጡ “የምሁር” ባንዶች ጫጫታ

ኢትዮጵያ በታሪኳ ምትክ ለሌላት ህያወታቸው ሳይሳሱ በዱር በገድሉ ከወራሪ ጠላቶች ጋር እየተናነቁ መስዋዕትነትን ከፍለው በነጻነት ተጠብቃ እንድትኖር ያበቋት ጅግኖች ልጆች ቢኖሯትም ጥቂት ለሆዳቸው ያደሩ ባንዶችና የጠላት እንቁላል አቅራቢዎችም አልታጡባትም። በአብይ አህመድ አዝማችነት በተለያዩ የኢትዮጵያ ግዛቶች ውስጥ በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ጀኖሳይድና የዘር ማጥፋት የሚያወገዙና አማራው የአጸፋውን እርምጃ እንዲወስድ የሚያስተባበሩ ትዕይነተ ህዝቦች ኢትዮጵያ ውስጥና በተለያዩ የዓለም ማዕዘናት መደረጋቸው ያስደነበራቸው ወዶ ገብ “የምሁር” ባንዶች እየተንጫጩ መሆናቸው ታውቋል። እነዚህ የምሁር ባንዳዎችን በመንዳት ላይ የሚገኘው ከዓለም ባንክ በስራ ችሎታ ማነስና በስነ ምግባር ጉድለት የተባረረው ዶ/ር ዮናስ ብሩ ሲሆን አብይ አህመድ እንደ ህወሃቱ አርከበ እቁባይ በኢንተርናሽናል ድርጅት ውስጥ ስራ እንዲያስቀጥረው ደጅ ጥናት ላይ መሆኑ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።

የአማራ ህዝብ ላይ ፋሽታዊ ጭፍጨፋና የዘር ማጥፋት እየተካሄድ ባለበት ጊዜ ገዳዩንና አራጁን አብይ አህመድን ማውገዝና ማጋለጥ እንዲሁም ጀኖሳይዱ እንዲቆምና ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ መታገል ሲገባ በተገላቢጦሹ “አገር አይፈርስም” በሚል ማጃጃያ ጭፍጨፋው እንዲቀጥል ውታፍ ነቃዮችና የአገዛዙ ተደጋፊዎች ህዝብን ለማወናበድ እየተርበደበዱ ይገኛሉ። ሆኖም የወገናቸው ደም መፍሰስ ያንገበገባቸው ምሁራን ደግሞ ለህዝብና ለአገር የሚጠቅም ተግባሮችን እያከናወኑ ይገኛሉ። ከነዚህ ምሁራን አንዱ አቶ ቲዎድሮስ አበበ በዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ላይ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ለፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጀኖሳይድ የትም ቢካሄድ ሊታወቅና ሊቆም ይገባል በማለት” ያስተላለፉትን ማሳሳቢያ ግንዛቤ እንዲሰጥ በማሰብ እዚህ ላይ አውጥተነዋል። የእንግሊዝኛውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ