በህወሓትና ኦነግ ሸኔ ላይ የተላለፈው የሽብርተኛነት የውሳኔ ሀሳብ የዘገየ ነው


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


May be an image of 1 person and text that says 'እንድ Ethiopian Press Agency 80+'“ሕወሓት እና ሸኔን ሽብርተኛ ብሎ መሰየም  አካፋን አካፋ የማለት ትክክለኛ ውሳኔ ነው“ ዶክተር አረጋዊ በርሄ የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር


(አሚኮ) ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) እና ሸኔን ሽብርተኛ ብሎ መሰየም አካፋን አካፋ የማለት ትክክለኛ ውሳኔ ነው ሲሉ የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር እና የህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ አስታወቁ ።

ህዝቡ ለራሱና ለአገሩ ጥቅም ሲል ተባብሮ በእነዚህ ሀይሎች ላይ መነሳት እንዳለበትም አመልክተዋል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው እለት ባካሄደው ስብሰባው፤ “ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት)” እና “ሸኔ” በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሃሳብ ማስተላለፉ፤ በዜጎች ላይ ሽብርን እየፈጸሙ፣ መሰረተ ልማቶችን እያወድሙና ህገ መንግስቱን እየጣሱ ያሉ ሀይሎችን በትክክለኛው ስማቸውና ግብራቸው ሽብርተኛ ብሎ መሰየም ነው ሲሉ ዶክተር አረጋዊ በርሄ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ተናግረዋል፡፡

በህወሓትና ሸኔ ላይ የተላለፈው የሽብርተኛነት የውሳኔ ሀሳብ የዘገየ ነው ያሉት ዶክተር አረጋዊ፤ በተለይ የህወሓት አመራሮች በበላይነት ይዘውት ከነበረው ስልጣን ተነስተው እኩል ሁኑ ሲባሉ ለፌዴራል መንግስቱ አንታዘዝም ሲሉ፤ ህገ መንግስቱና የምርጫ ቦርድ የማይፈቅደውን ምርጫ ሲያካሄዱና በአገር መካላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ሲሰነዝሩ ሽብርተኛ ተብለው ሊሰየሙ ይገባ ነበር ብለዋል።

እነዚህ ሁለቱ ጸረ ሰላም ሀይሎች በዜጎች ላይ ሽብርን የሚፈጸሙ፣ መሰረተ ልማትን የሚያወድሙና ህገ መንግስቱን የሚጥሱ በመሆኑ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ብሎ ውሳኔ ማስተላለፉ አካፋን አካፋ የማለት አስፈላጊ ውሳኔ ነው ብለዋል፡፡

የህወሓት አመራሮች የአገር ደጀን በሆነው የአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት በመሰንዘር ሽብር ብቻ ሳይሆን የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጸመው እንኳን እስካሁን ድረስ ትክክለኛ ፍረጃ እንዳልተሰጣቸው አስታውቀዋል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በህወሓትና በሸኔ ላይ ያስተላፈው ውሳኔውን ሙሉ በሙሉ ከእነምክንያቱ የምንደግፈው ነው ያሉት ዶክተር አረጋዊ ፤ ይችን አገር ለማፍረስ ህዝቡን ወደ ጦርነት ውስጥ ለመክተት እየተቀሳቀሱ ያሉ ሀይሎች ናቸው ብለዋል፡፡

በተለይ የህወሓት አመራሮች ለውጡን አንቀበልም፣ በነበርንበት ስልጣን በስርቆት፣ በማጭበርበርና በአፈና መቆየት አለብን በሚል አሻፈረኝ ማለታቸውን አስታውሰው፤ ሁለቱ ጸረ ሰላም ሀይሎች በመላው ኢትዮጵያ ችግር እየፈጠሩ መሆኑን ገልጸው፤ በተለይ የህወሓት አመራሮች በትግራይ ህዝብ ላይ ይቅር የማይበል የህዝብ እልቂት እያካሄዱ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

እነዚህ ሀይሎች ህዝብን እያጠቁ ብቻ ሳይሆን መሰረተልማቶች፣የመንግስት መዋቅሮችና ግንባታዎችን እያፈረሱ ናቸው፤ ህዳሴው ግድብንም የማይሆን ነገር ቢሆንም እናፈርሰዋለን እያሉ እየዛቱ ናቸው፤ እነዚህ ሀይሎችን በሽበርተኝነት መፈረጅ ተገቢ ነው ብለዋል፣

ቡድኖቹ በሽብርተኝነት መፈረጃቸው ህዝቡ እኩይ ድርጊታቸውን አውቆ በእነዚህ የሽብር አባወራዎች ላይ ተባብሮ እርምጃ እንዲወስድባቸው ያስችላል ያሉት ዶክተር አረጋዊ፣ ህዝቡ ለራሱና ለአገሩ ጥቅም ሲል ተባብሮ በእነዚህ ሀይሎች ላይ መነሳት እንዳለበት ማሳሰባቸውን የዘገበው ኢፕድ ነው፡፡