ኦነግ ሸኔን በ15 ቀን ውስጥ ድባቅ መትቼ ክልሉን ሠላም ለማድረግ እየሰራሁ ነው – የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ኦነግ ሸኔን በ15 ቀን ውስጥ ድባቅ መትቼ ክልሉን ሠላም ለማድረግ እየሰራሁ ነው አለ፡፡

ለዚህም የክልሉ መንግሥት የፀጥታ ሃይል ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጋር ተቀናጅተው ቡድኑ ላይ እርምጃ እየወሰደ ነው፤ ውጤትም እየተመዘገበ ነው ሲሉ ወሬውን ለሸገር የነገሩት የክልሉ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ናቸው፡፡

እስከ አሁንም 41 የኦነግ ሸኔ አባላት መገደላቸውን፤የተማረኩ እና የቆሰሉ መኖራቸውን አቶ ጌታቸው ነግረውናል፡፡ የቡድኑን አባላት በመደምሰሱ ዘመቻ ሃላፊነቱን ተባባሪ ሆነው የተገኙ እና ሃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ የመንግሥት አመራሮችም፤ ከመጠየቅ እንደማያመልጡ የቢሮ ሃላፊው ተናግረዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት በምዕራብ ኦሮሚያ ባቦ ጋምቤል አካባቢ የተፈጠረውን ግድያ ተከትሎ ማህበረሰቡ በየአካባቢው የተጠናከረ ጥበቃ እያደረገ እንደሚገኝም ሠምተናል፡፡

የኦሮሚያና የአማራ ከልሎች ከፍተኛ አመራሮች በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ምክር አድርገዋል፡፡ በምክክሩ የሁለቱን ክልሎች ህዝቦች አብሮነት በማጠናከር የሀገርን አንድነት ማስቀጠል ስለሚቻልበት ጉዳይ ውይይት ተደርጓል ተብሏል፡፡ በድንበር አካባቢ የሚከናወኑ የልማት ስራዎች ጉዳይም በምክክሩ ተነስቶ አጠቀላይ መግባባት ላይ ተደርሷል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ – ሸገር