ግብጽ ፈርጣጭና ፈሪ ነች ባደረገችው ጦርነት አንዴም አሸንፍ አታውቅም


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ግብፅ ከአስዋን ግድብ በስተ ምስራቅ በሚገኘው ሰሜናዊ የቀይ ባህር ዳርቻ Berenice Military Base በአፍሪካ ታላቅ የሚባለውን የጦር ካምፕ ገንብታ አስመርቃለች። በደቡብ ምስራቅ ግብፅ ቀይ ባህር ላይ ያለ በዘመነ ወታደራዊ ኃይል የተሞላ ነው። አየር ኃይሉ እያንዳንዳቸው 3000 ሜትር ርዝመት፤ ከ30 እስከ 45 ሜትር ስፋት ያላቸው ማንኮብኮቢያዎች አሉት፡፡ የባህር ኃይሉ 1000 ሜትር ርዝመት ወደብና 14 ሜትር ጥልቀት አለው፡፡ አውሮፕላን ተሸካሚ ሃንጋርና የባሕር ሰርጓጅ መርከቦች የመያዝ መስፈርቶችን ያሟላ ካምፕ ነው። ሆኖም ግን ከኢትዮጵያ ሰሜናዊ ድንበር ጫፍ 2200 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት አለው።
የግብፅ አየር ኃይል 10 ሺህ ተዋጊዎች እና ሌሎች 50 ሺህ ወታደራዊ ሃይሎች አለው። ግብፅ 220 የአሜሪካ F-16 የጦር አውሮፕላኖችና በርካታ በአሜሪካ የተሰሩ ለቅርበት ውጊያ የሚሆኑ ሄሊኮፕተሮች አሏት። በአየር ኃይል ብቻ ግብፅ ከቱርክ፣ ከእስራኤል፣ ከኢራንና በጠቅላላ ከመካከለኛው ምስራቅ እና በሰሜን አፍሪካ የላቀ ሃያል አየር ኃይል አላት። ጠቅላላ የጦር አውሮፕላኖቿ ቁጥሩ 1092 ነው። (GFP) Global Fire Power እ.ኤ.አ. በ2018 ባደረገው አለም አቀፍ ዳሰሳ ግብፅ ከዓለም 10ኛ ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል ደረጃን ይዛለች፡፡ በአፍሪካ አህጉር ወደር የሌለው አየር ኃይል ነው።
ታሪካዊ ጠላታችን ግብፅ ኢትዮጵያ ላይ ወታደራዊ ጥቃት ማድረስ ትችላለች? ለምሳሌ የግብፅ F-16 ከ860 ኪሎ ሜትር መብረር፣ መሣሪያዎቹን ትክክለኛ ኢላማ መተኮስ፣ ከጠላት አውሮፕላን መከላከል እና ወደ መነሻው መመለስ ይችላል፡፡ ሆኖም ግብፅ ከኢትዮጵያ ካላት ርቀት የF-16 ጥቃት አይታሰብም።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል 48 የጦር አውሮፕላኖች፣ በሩሲያ የተሰሩ የውጊያ ሄሊኮፕተሮች አሉት። ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ ለመግዛት የተስማማችው 12 የውጊያ አውሮፕላኖች፣ 18 ሄሊኮፕተሮች ናቸው። ምናልባት የኢትዮጵያ ወታደራዊ ሃይልን የተሻለ የሚያደርገው 6 ሺህ ኪሎ ሜትር ኢላማ መምታት አቅም ያላቸው ሰላሳ M51 ሚሳዬሎች ከፈረንሳይ መገዛታቸው ነው። ከአዲስ አበባ ካይሮ 3300 ኪሎ ሜትር ገደማ ነው። ጦርነት ቀላል ነገር አይደለም። ሆኖም ግን በጥቂት መሳሪያ ግብፅን የሚመጥን ወታደራዊ ኃይል አለን።
ግብፅ ያሏት ሚሳዬሎች R-300 (SS-1-C Scud-B) 300 ኪሎ ሜትር Project-T (Scud B-100) 450 ኪሎ ሜትር Scud-C 550 ኪሎ ሜትር R-70 Luna M (Frog-7B) 70 ኪሎ ሜትር። በአጠቃላይ ከ70 እስከ 550 ኪሎ ሜትር ብቻ የሚምዘገዘጉ ሚሳዬሎች ናቸው።
ግብፅን መፍራት አለብን? የለብንም። ኮንቬንሽናል ጦርነት ሊኖር አይችልም። ጦርነት ከፈለጉም ሳይዋጉን ይሸነፋሉ። እኛ አንድ ሀገራዊ አቋም ይዘን ሕዳሴን ሰርተን መጨረስ አለብን። ግብፅ ድንጋይ ስትቆልል የኖረች ሃገር ናት። ከፈርዖን ዘመን ጀምሮ አንድም ጦርነት አሸንፋ አታውቅም።