በደቡብ ክልል የታጠቁ ቡድኖች በተለያዩ ቀናት በፈጸሙት ጥቃት 12 ሰዎች ተገድለው ከ11 ሺ በላይ ሰዎች ተፈናቀሉ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች የታጠቁ ቡድኖች በተለያዩ ቀናት በፈጸሙት ጥቃት 12 ሰዎች ተገድለው፣ ከ11 ሺ በላይ መፈናቀላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ታጣቂዎቹ እያደረሱ ባለው ጥቃት ፣ ግድያና ዘረፋ ህልውናችን በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቸ ቬለተናግረዋል። ታጣቃዊዎቹ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በልዩ ወረዳው የተለያዩ ቀበሌያት በመዘዋወር ባደረሷቸው ጥቃቶች በሰዎች ላይ ካደረሷቸው ግድያ በተጨማሪ በንብረትም ላይ እያደረሱ ባለው ውድመት የመኖርያ ቄዬአቸውን ለቀው ለመሰደድ መገደዳቸውን ነዋሪዎች ጨምረው ገልጸዋል። DW