ሱዳን በአብዬ ግዛት የሚገኘው የኢትዮጵያ ሰላም አስካባሪ ኃይል ከቦታው ለቆ እንዲወጣ ተመድን መጠየቋን በይፋ አስታውቃለች፡፡


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ሱዳን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ከአብዬ እንዲወጣ ጠየቀች።

ሱዳን በአብዬ ግዛት የሚገኘው የኢትዮጵያ ሰላም አስካባሪ ኃይል ከቦታው ለቆ እንዲወጣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን(ተመድ) መጠየቋን አስታውቃለች፡፡

ሱዳን ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰቸው በኪንሻሳ የተካሄደው የግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ያለስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው።

የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር ከአብዬ ግዛት እንዲወጣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር እየተነጋገሩ መሆኑንም ሱዳን ገልጻለች። የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል በተመድ ስር በመሆን በሱዳንና በደቡብ ሱዳን መካከል በምትገኘውና ሁለቱ ሀገራት ይገባኛል ጥያቄ የሚያቀርቡባት አብየ ግዛት በፈረንጆቹ በ2011 ጀምሮ ሰላም ለማስከበር ሰፍሮ ቆይቷል፡፡

አብዬ ግዛት በነዳጅ እና ሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶች የበለጸገች ግዛት ናት። በዚህም ምክንያት ደቡብ ሱዳን ነጻነቷን እንደ በፈረንጆቹ በ2011 ነጻነቷን መቀዳጀቷን ተከትሎ ነበር ሁለቱ ሀገራት ወደ ግጭት ያመሩት።

በሁለቱ ሀገራት መልካም ፈቃድ፣ ኢትዮጵያ በዚች ግዛት ሰላም እንዲሰፍን ከ4 ሺህ በላይ ጦር ወደ ሰፍራው አቅነቶ ሰላም በማስከበር ላይ ይገኛል።

ኢትዮጵያ ሱዳን እና ግብጽ በሱዳን በኪንሻሳ የተካሄደው የግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ያለስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ ሱዳን በአብዬ ግዛት ያለው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር እንዲወጣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ መሬም አልሳዲግ አልመሀዲ በኩል አስታውቃለች።

በአብዬ ግዛት ላይ በተሰማራው የኢትዮጵያ ሰራዊት ላይ እምነት የለንም ያሉት ሚኒስትሯ ጦሩ በፍጥነት አብዬን ለቆ እንዲወጣ እንፈልጋለንም ብለዋል።

እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ ኢትዮጵያ በድርድሩ ላይ ግትር አቋም አሳይታለች፤ በኬንሻሳ የተካሄደው የሶሰትዮሽ ድርድር ያለስምምነት የተጠናቀቀው ኢትዮጵያ ስላልፈለገች ነው።

ሚኒስትሯ አክለውም ኢትዮጵያ በሱዳን ላይ ብዙ ፍላጎት አላት ፤ሱዳን ጥቅሟን ለማስከበር ብዙ አማራጮችን ትጠቀማለች ብለዋል።

ኢትዮጵያ ያለችበትን የውስጥ ችግር ሱዳን ተረድታ ለረጅም ጊዜ ታግሳለች፤በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ተቀብለናል ያሉት ሚኒስትሯ ከእንግዲህ ግን ይህ ያበቃል በቀጥታ ብሔራዊ ጥቅማችንን ማስከበር ላይ እናተኩራለን ሲሉ በኬንሻሳ ተናግረዋል።

አል ዓይን ኒውስ