ኦነግ ሸኔ የተባለን ሸማቂ ቡድን በገንዘብና በሃሳብ በመደገፍ መንግሥትን ለመገልበጥ አሲረዋል በሚል የጂማ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞች ተከሰሱ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


DW : ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ 10 የጂማ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞች ሕዝብን ለሁከት በማነሳሳት፣«ኦነግ ሸኔ» የተባለን ሸማቂ ቡድን በገንዘብና በሃሳብ በመደገፍ መንግሥትን ለመገልበጥ አሲረዋል በሚል መጠርጠራቸውን የአንዱ ቤተሰብ ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። ባለፈው ዓርብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት 8 የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ሠራተኞችን ጨምሮ ዛሬ በከተማዋ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተሰየመው ችሎት የቀረቡት 10 ተጠርጣሪዎች ላይ የተመሰረተው ክስ ፖሊስ መረጃውን ለማጠናቀር ከጠየቀው 14 ቀናት 10ሩ ተፈቅዶ ለሚያዚያ 07 ቀን 2013 ተለዋጭ ቀጠሮ መያዙ ነው የተገለጸው። ከተጠርጣሪዎቹ የዩንቨርሲቲው የቀድሞ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት እና የአሁኑ የዩኒቨርሲቲው የጥናትና ልማት ኃላፊ ይገኙበታል። በሌላ በኩል የጂማ ዩኒቨርሲቲ ከወራት በፊት የ2012 ዓ.ም. ተመራቂ ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ወደ መድረክ ወጥቶ እነ አቶ ጃዋር መሃመድ እና ሌሎች ይፈቱ ሲል የተናገረውና በሌሎች ወንጀሎች መጠርጠሩ ተገልፆ የነበረው መሃመድ ዴክሲሶ አሁን ላይ የት እንዳለ እንደማያውቁ ወንድሙ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡