ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በታጣቂዎች በተፈፀመ ሌላ ጥቃት የሰው ሕይወት መጥፋቱ ተሰማ

  • ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ደንጎሮ እና ቢላ ወረዳዎች በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት የሰው ሕይወት መጥፋቱን የአካባቢው ነዋሪዎችና የዞኑ አስተዳደር አመልክተዋል።
  • ከሆሮጉድሩ ወለጋ የተፈናቀሉት ወገኖች ከመንግሥት ተገቢው ድጋፍ እየተደረገልን አይደለም ሲሉ አመለከቱ።

DW : ከኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ከተለያዩ ወረዳዎች በማንነታቸው ምክንያት የሚደርስባቸውን ጥቃት በመፍራት በአማራ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮች ከመንግሥት ተገቢው ድጋፍ እየተደረገልን አይደለም ሲሉ አመለከቱ። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው ተፈናቃዮች እንደሚሉት እስካሁን የአካባቢው ነዋሪ በሚያደርግላቸው ድጋፍ ነው ኑሯቸውን ለመግፋት የተገደዱት። በተጠቀሰው አካባቢ ከአንድ ኂህ የሚበልጡ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ ያመለከቱት በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የተሁለደሬ ወረዳ ግብርና ልማት ባልደረባ በበኩላቸው ከመንግሥት ለተፈናቃዮቹ የተደረገው በቂ አይደለም ይላሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለም ትናንት በዚሁ ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ደንጎሮ እና ቢላ ወረዳዎች በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት የሰው ሕይወት መጥፋቱን የአካባቢው ነዋሪዎችና የዞኑ አስተዳደር አመልክተዋል።