በትግራይ ሰላም እንዲወርድ ቫቲካን ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ጥሪ አቀረቡ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኢትዮጵያ ትግራይ እና የሞዛምቢክ ካቦ ዴልጋዶ ክልሎችን ጨምሮ ግጭት በበረታባቸው አካባቢዎች ሰላም እንዲወርድ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ሊቃነ-ጳጳስ ፍራንሲስ ጥሪ አቀረቡ።

ሊቃነ-ጳጳስ ፍራንሲስ ዛሬ የሚከበረውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክት የየመን ቀውስ ጆሮ ዳባ ልበስ ተብሏል ሲሉ ተችተዋል። በመፈንቅለ-መንግሥት በምትታመሰው እና ከጥር 24 ወዲህ ከ550 በላይ ተቃዋሚዎች በተገደሉባት ምያንማር ወጣቶች ዴሞክራሲን ለመደገፍ እና ድምፃቸውን በሰላማዊ መንገድ ለማሰማት ያላቸውን ቁርጠኝነት አድንቀዋል።ለወትሮው በቫቲካን አደባባይ ከቤተ-ክርስቲያኒቱ ደጃፍ እስከ 100,000 የሚደርሱ ምዕምናን የፍራንሲስን የፋሲካ መልዕክት ያደምጡ የነበረ ቢሆንም ዘንድሮ ግን በወረርሽኙ ምክንያት የታደሙት ከ200 ያልበለጡ ሰዎች ናቸው። በኮሮና ሳቢያ የፋሲካ ክብረ በዓል ታዳሚዎች ቁጥር ሲገደብ ሁለተኛው መሆኑ ነው። የኮሮና “ወረርሽኝ አሁንም እየተስፋፋ ነው።

ማህበራዊ እና ምጣኔ-ሐብታዊ ቀውሱም በተለይ ለድሆች እንደበረታ ነው” ያሉት ፍራንሲስ ግጭቶች እና ውጊያዎች ሳይቆሙ ለጦር መሣሪያ ግዢ የሚውለው ገንዘብ መጨመሩን ጠቅሰው “አሳፋሪ” ብለውታል። “ጦርነት በዝቷል፤ ኹከትም በርትቷል” ያሉት ፍራንሲስ ለመፍትሔ ፈጣሪያቸውን ተማጽነዋል። ዓለም የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ሥርጭት ለገጠመው መዘግየት መፍትሔ እንዲያፈላልግ በተለይም ለደሐ አገሮች የሚዳረስበትን መንገድ እንዲያመቻች ፍራንሲስ አሳስበዋል።