ትግራይ ክልል ከመንግሥት በተጨማሪ ከ75 በላይ ዓለም አቀፍ ተቋማት እየሰሩ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


  • ሱዳን በህገወጥ መንገድ ከያዘችው መሬት የምትወጣ ከሆነ ኢትዮጵያ ለድርድር ዝግጁ መሆኗንም አስታውቃለች።
  • ትግራይ ክልል ከመንግሥት በተጨማሪ ከ75 በላይ ዓለም አቀፍ ተቋማት እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
  • የህዳሴው ግድብ ውይይትን በተመለከተም ኢትዮጵያ ሌላ አደራዳሪ እንደማትፈልግም አምባሳደር ዲና አስታውቀዋል ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የሱዳን ወታደራዊ ክንፍ የያዘውን መሬት ለቆ በፊት ወደነበረበት ቦታ ከተመለሰ ኢትዮጵያ ትደራደራለች ብሏል።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በዚህ ወቅት እንዳሉት ሱዳን የያዘችውን መሬት በለቀቀችበት ቅፅበት ኢትዮጵያ ወደ ውይይት ትመለሳለች በወቅታዊ ጉዳዮች መግለጫ ላይ ብለዋል።በርካታ የጎረቤትና ሌሎች የአለም አገራት እናስታርቃችሁ የሚል ጥያቄ እና ፍላጎት እንዳላቸው የገለፁት አምባሳደር ዲና ይህ ግን ሊታይ የሚችለው ሱዳን ወደነበራት ይዞታ ስትመለስ ብቻ ነው ብለዋል።

ከትግራይ ክልል ጋር በተያያዘም ከመንግሥት በተጨማሪ ከ75 በላይ ዓለም አቀፍ ተቋማት እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡በዚህም በትግራይ ክልል 36 ወረዳዎች በ92 የዕርዳታ ማከፋፈያ ጣቢያዎች የሚደረገው ድጋፍ 70 በመቶው በመንግሥት ቀሪው ደግሞ በዓለም አቀፍ ተቋማት የሚሸፈን መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

May be an image of 1 person and sitting

ኢትዮጵያ ቱርክን ከሱዳን ጋር አሸማግሊኝ ብላ ጠይቃለች ተብሎ የሚወራ ከእውነት የራቀ ነውም ተብሏል።

የኢትዮ ሱዳን የድንበር ውዝግብ የሁለቱ አገራት ጉዳይ በመሆኑ ችግሩን መፍታት የሚገባው በሶስተኛ ወገን ሳይሆን በባለጉዳዮቹ እንደሆነም ቃል አቀባዩ አንስተዋል።

በሌላ በኩል የህዳሴው ግድብ ውይይትን በተመለከተም ኢትዮጵያ ሌላ አደራዳሪ እንደማትፈልግም አምባሳደር ዲና አስታውቀዋል ።

የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት ክንፍ ከመቶ ዓመት በላይ የቆየውን የድንበር ጉዳይ በሰሜን ኢትዮጵያ ችግር ሲፈጠር እንደ አዲስ ማንሳቷ ለሶስተኛ ወገን ጥቅም ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ዲፕሎማሲ፣ በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲና በሰሜን ኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

አምባሳደር ዲና እንዳሉት የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት ክንፍ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ መግባት የሁለቱንም አገራት ሕዝብ አይጠቅምም፡፡

ሱዳን ከመቶ ዓመት በላይ የቆየውን የድንበር ጉዳይ በሰሜን ኢትዮጵያ ችግር በተፈጠረበት ወቅት ማንሳቷ የሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት እንዳለ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

የሱዳን ያልተገባ አካሄድ አሁንም መፈታት ያለበት ሱዳን የያዘችውን የኢትዮጵያን መሬት ለቃ ስትወጣ በሚደረግ ድርድር እንደሆነ ፅኑ አቋም አለን ብለዋል፡፡

ከትግራይ ክልል ጋር በተያያዘም ከመንግሥት በተጨማሪ ከ75 በላይ ዓለም አቀፍ ተቋማት እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በዚህም በትግራይ ክልል 36 ወረዳዎች በ92 የዕርዳታ ማከፋፈያ ጣቢያዎች የሚደረገው ድጋፍ 70 በመቶው በመንግሥት ቀሪው ደግሞ በዓለም አቀፍ ተቋማት የሚሸፈን መሆኑን ጠቁመዋል፡፡