በፓርቲ አባላትና አስተባባሪዎች ላይ የሚደረግ እስራት አሁንም አልተቋጨም – በምርጫ እንድሳተፍ የሚፈቅድ አውድ የለም፡፡


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


  • በምርጫ እንድሳተፍ የሚፈቅድ አውድ የለም – ኦፌኮ 
  • ኦፌኮ እስካሁን አንድም እጩ ተወዳዳሪ አላስመዘገበም

በዓመቱ ማገባደጃ ለሚደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ የእጩዎች ምዝገባ ቀነ ገደብ ከሳምንት ያነሰ ጊዜ ቢቀረውም እስካሁን አንድም እጩ ተወዳዳሪ አለማስመዝገቡን የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦ.ፌ.ኮ) አስታወቀ፡፡ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ በተለይም ለዶይቼ ቬለ እንዳሉት በፓርቲው አባላትና አስተባባሪዎች ላይ የሚደረግ እስራት አሁንም አልተቋጨም፡፡ በየአከባቢው የሚገኙ ጽሕፈት ቤቶችም በከፊል ሲዘጉ ክፍት በሆኑትም በተረጋጋ መልኩ የምርጫ ቅስቀሳ እና ሌሎች ተግባራትን መተግበር አለመቻሉንም ፓርቲው አክሎ ገልጧል፡፡  ገዢው ብልፅግና ፓርቲ በበኩሉ ምርጫውን ሰላማዊና ነጻ አውድ የሚስተዋልበት እንዲሆን ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡