የምርጫ ቦርድ ኢፍትሃዊ የምርጫ ድልድል ፣ በቢኔሻንጉል #ግርማካሳ

የሕዝብ ቆጠራ የተደረገው እንደ ግሪጎሪያኑ አቆጣጠር በ2007 ዓ/ም ነው፡፡ ከአስራ አራት አመት በፊት፡፡ በወቅቱ በተደረገው የህዝብ ቆጠራ ብዙ ስህተተኦችን ግድፈቶች እንደነበሩት በወቅቱ በስፋት የተዘገበ ጉዳይ ነው፡፡ በተለይም የአማራ ክልል ህዝብ ቁጥር ከ2 እስከ 3 ሚሊዮን እንዲቀንስ መደረጉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሳይቀር ጥይቄዎች ያስነሳና ጉዳይ ነበር፡፡
እንደዚያውም ሆኖ ያለፈውን ምርጫ ስንመለከተ በቢኔሻንጉል ክልል 786345 የሚሆን ሕዝብ እንደነበረ ነው የተቀመጠው፡፡ ከነዚህ መካከል በአሶሳ ዞንና በማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ 360885 (45%) በፓዌ ልዩ ወረዳና በመተከል ዞን 321919 (42%) እንዲሁም በከማሺ ዞን 101543 (13%) የሚሆን ሕዝብ እንደሚኖር ነው የሚታወቀው፡፡
ከቤኒሻጉልል ክልል 9 የፓርላማ እንዲሁም 99 የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች ነው ውድድር የሚደረገው፡፡
ምርጫ ቦርድ መጪውን ምርጫ በተመለከተ በመጀመሪያ በሺሆች የሚቆጠሩ ዜጎች ተፈናቅለው ባለበት ሁኔታ ምርጫ ለማድረግ ማሰቡ በራሱ ኢሞራል ብቻ ሳይሆን የሚወገዝ ነው፡፡ መቅደም የነበረበት ምርጫ ሳይሆን ዜጎች ወደ ቅያቸው እንዲመለሱ ማድረግ ነበር፡፡ ያ አልሆነወ፡፡ ሰብአዊነት መቅደም አልቻለም፡፡በጣም ያሳዝናል፡፡
እንደዚያም ሆኖ ምርጫ ቦርድ ፣ የምርጫ አከላለኖችን ድልድል ሲያደርግ ፍጹም ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ ነው ያደረገው፡፡ በመረጃ በአንድ በኩል የሕዝብ ቆጠራ ውጤትን ፣ በሌላ በኩል የምርጫ ቦርድ መግለጫን በማነጻጸር ለማስረዳት እሞክራልሁ፡፡
ማኦ ኮሞ ልዩና ወረዳና አሶሳ ዞን 45% የህዝብ ብዛት ቁጥር ሲኖራቸው ለፓርላማ 6 ወይንም 67% ፣ ለክልል 50 ወይንም 50% እጩዎችን ያስመርጣሉ፡፡ ከማሺ ዞን 13% ሲሆን፣ አንድ ወይንም 11% ለፓርላማ፣ 16 ወይንም 16% ለክልል እጩዎች ያስመርጣሉ፡፡ በአንጻሩ መተከልና ፓዌ 43% ሲሆኑ ከፓርላማ መቀመጫዎች 2 ወይንም 22% ፣ ለክልል ደግሞ 33 ወይንም 33% ብቻ ነው የሚያስመርጡት፡፡
በወረዳ ደረጃ ስንሄድ በአሳሳ ዞን የባብማሲ ወረዳ 48 ሺህ፣ የሰርብ አባይ ወረዳ 17 ሺህ ፣ የማኦኮ ልዩ ወረዳ 50 ሺህ ሰው እያላቸው እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ወረዳ ለፓርላማ ያሰለፋሉ፡፡ በአንጻሩ በመተከለ ያሉት ለምስላኡእ የድባጤ ወረዳ 66 ሺህ የወምበራ ወረዳ 60 ሺህ እንዲሁም ፓዌ 48 ሺህ እየኖረባቸው አንድ ተወካይ እንዲመርጡ አልተደረገም፡፡
እንግዲህ ከዚህ የበለጠ ፈጦ የወጣ ኢፍትሃዊ አሰራር የለም፡፡ ምርጫ ቦርድ ቢያንስ የሕዝብ ቆጠራ መደረግ ነበረበት ብሎ መከራከር ባይችልም ከዚህ በፌት የተደረጉት የህዝብ ቆጠራ ከግምት ማስገባት ነበረበት፡፡
በኔ ግምት አንደኛ አሁን በቢኔሻንጉል ምርጫ የሚደረግበት ጊዜ ስላልሆነ ፣ ሁለተኛም እንደዚህ አይነት ከፍተኛ ግድፈቶችና ኢፍትሃዊነቶች ስላሉ ምርጫ ቦርድ የቢኔሻንጉል ክልል ምርጫን ማራዘም ነው ያለበት፡፡