የእጩዎች ምዝገባ የካቲት 21 እንደሚጠናቀቅ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በአዲስ አበባ ከተማ እና በድሬዳዋ ከተማ መስተዳደር ፣ በቤኒሻንጉል፣ በሃረሪ፣ በጋምቤላ እና ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልሎች የእጩዎች ምዝገባ የሚጠናቀቀው የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑን ገለጸ።

ይህንንም አውቃችሁ የጊዜ ገደቡ ከማለፉ በፊት የእጩዎች ምዝገባ እንድታጠናቀቁ ጥሪያችንን እናቀርባለን ሲል ቦርዱ አስታውቋል።

ቦርዱ አያይዞም በአዲስ አበባ መስተዳድር የሚገኙ የምርጫ ክልል ቢሮዎችን ዝርዝር የመገኛ አድራሻ ለማግኘት የሚፈልጉ ሁሉም የፓለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ቦርዱ የፌስ ቡክ ገጽ ላይ ከዜናው ስር በሚገኘው ማስፈንጠሪያ በመጫን ዝርዝር አድራሻውን ማየት እንደሚችሉ ገልጿል።

በተጨማሪ ም አስፈጻሚዎችን ለማነጋገር የሚፈልጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ካሉ ደግሞ አድራሻቸውን ከቦርዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የስራ ክፍል መውሰድ የሚችሉ መሆኑን ቦርዱ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ አስቀምጧል።

Source – ምርጫ ቦርድ