“ኢትዮጵያ እና ጾመ ነነዌ” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


“ኢትዮጵያና ጾመ ነነዌ” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ከነገ ጀምሮ ለሶስት ቀናት የምትጾመውን ጾመ ነነዌ አስመልክተው ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ቀደም ብለው ኢትዮጵያና ጾመ ነነዌ” በሚል ርዕስ የሰጡት ትምህርተ ወንጌል ለአሁኑ ጊዜም እጅግ አስፈላጊ ስለሆነ በድጋሚ አቅርበንላችኋል። የኢትዮጵያ ነገር “አድሮ ቃሪያ ወይም ከርሞ ጥጃ” እየሆነ በመምጣቱ ህዝቡ የተሻለ ነገር ቢጠብቅም የባሰ እየመጣበት አሳርና መከራውን እየከፈለ ይገኛል። በተለይም ካለፉት ሶስት ዓመታት አንስቶ “ለውጥ” መጣ እየተባለ የውሸት ከበሮ ቢደለቅም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ እየወረደባት ያለው መከራ በታሪኳ ምናልባትም በግራኝ አህመድ ወረራ ጊዜ ወይም በዮዲት ጉዲት ጊዜ ከደረሰው ጋር ሲወዳዳር በማይተናነስ መልኩ እንደ ጠላት ተቆጥራ ተዘምቶባታል። በርካታ የቤተክርስቲያኒቷ ምዕመናን በግፍ ተጨፍጭፈዋል፣ ቤተክርስቲያናት በእሳት ጋይተዋል፣ምዕመናን ከሶስትና አራት ትውልድ በላይ ከኖሩበት መንደራቸው እንዲሰደዱና ሜዳ ላይ የጅብ እራት አንዲሆኑ ተደርገዋል። ተደፍረው የማያውቁ ታላላቅና ጥንታዊ ገዳማት እንደ ደብረ ዳሞና አክሱም ጽዮን ዓይነቶች ተዘርፈው ምዕመናን በባዕዳን ወታደሮች ጭምር እንዲጨፈጨፉ ተደርገዋል።

ማተብ አንገት ላይ ማድረግ ከስራ የሚያስባርርና የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ያለበት ነጠላ መልበስ ወይም ከበሮ መያዝ የሚስገድል ወንጀል ሆኗል። ይህንንና ከዚህም የባሰ ጭፍጨፋና ጦርነት ተከፍቶባት ምዕመናኖቿ ከሞቱ በኋላ እንኳን አፈር እንዳይለብሱ አስከሬናቸው እንደ ቁሻሻ በግሬድር ጭነት መኪና ላይ እየተጫነ በጅምላ ጉድጓድ ውስጥ እንዲጣሉ ተደርገዋል። እርጉዝ ሴቶች በማህጸናቸው ያረገዙት ሽል ሆዳቸው በሳንጃ እየተዘነጠለ ሜዳ ላይ ተጥሏል። እንደዚህ ዓይነት ግፍ በማንኛውም ህዝብ ላይ ተፈጽሞ አያውቅም። ይህ የሚያሳየው የወቅቱ የአገሪቷ ገዥዎች ምን ያህል ጥላቻ ለኦርቶዶክ ተዋህዶ እንዳላቸው ነው።

በቤተክርስቲያኒቷ ላይ ከዚህስ የከፋ ምን ሊደርስባት ይችላል? በኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን አማኞች ላይ እየደረሰ ያለው ስቃይ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም። ለማንኛውም የቤተክርስቲያኒቷ አማኞች እየደረሰባቸው ያለው ጭፍጨፋ በፊትም አያቶቻቸውና ቅድም-አያቶቻቸው ላይ የደረሰና በፅናትና በአንድነት በመቆም እንደተወጡትና ጠላቶቻቸውን ድል እንደነሱ አምነው ከአራጆቻቸው ጋር ተፋልመው መብታቸውንና ህልውናቸውን ማስከበር አለባቸው። ክርስትና በእምነት ብቻ ሳይሆን በስራም መገለጽ ስላለበትና ካለመስዋዕትነት የሚመጣ ስርየት፣ሰላምና ደህነት ስለሌለ ሁሉም ምዕመን በዚህ የነነዌ ጾም በኦርቶዶክስ ምዕመናን ላይ እየደረሰ ያለውን ጭፍጨፋ ለማስቆም ምን ማድረግ እችላላሁ የሚለውን አብሮ ሊያስብበት ይገባል እንላለን።