መተከል በድባጤ ወረዳ ጋሌሳ ቀበሌ ሌላ ጥፋት ለማድረስ የተዘጋጁ ቡድኖች በዙሪያው ይገኛሉ ተባለ

Image may contain: one or more people and outdoorየተገደሉትን የመተከል ነዋሪዎች ምስሎች ከታች ያገኙታል !

መተከል ዞን በወረዳው በዳሊቲ፣ ጋሌሳና ቆርቃ ቀበሌ ቁጥራቸው የበዛ ንጹሓን መገደላቸው ነው የተነገረው። የተለያዩ ሚዲያዎች የተለያየ ቁጥር ቢያወጡም ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ ከመቶ ያላነሱ ሰዎች ሞት ተሰምቷል። (የሟቾች ቁጥር በሚመለከተው አካል እስካሁን አልተረጋገጠም)

በዞኑ የተቋቋመው አዲስ ግብረ ሃይል በንጹሃን ዜጎች ላይ ጥቃት እየፈፀመ ባለው የጥፋት ቡድን ላይ የተጠናከረ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ገልጿል።

ይሁንና የጥፋት ቡድኑ በአንዳንድ አካባቢዎች የተስፋ መቁረጥ ጥቃት መፈጸሙን የገለጹት በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ በእነዚህ አካባቢዎች የፀጥታ ሃይሉ በአፋጣኝ በመድረስ በቡድኑ ላይ እርምጃ መውሰዱን ተናግረዋል።

አሁንም በድባጤ ወረዳ ጋሌሳ ቀበሌ ሌላ ጥፋት ለማድርስ የተዘጋጁ ቡድኖች በዙሪያው እንደሚገኙና እንዳሳሰባቸው መናገራቸውንና በከባድ ጭንቅ ውስጥ ሆነው የድርሱልን ጥሪም አቅርበዋል ሲል አብመድ ዘግቧል።

Image may contain: 1 person, outdoor

በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ በደረሰ ጥቃት ንፁሃን መገደላቸውን የዓይን እማኞች ለኢቲቪ በስልክ ገለፁ።በጥቃቱ ህፃናት እና ሴቶች በብዛት ሰለባ መሆናቸውንም ነው የዓይን እማኞቹ የተናገሩት።ከጥቃቱ የተረፉትን ወገኖች ለማዳን መንግስት የአንቡላንስ፣ የሰብአዊ እርዳታ እና የድንገተኛ ህክምና ባለሙያዎችን ወደ አካባቢው እንዲያሰማራም ነዎሪዎቹ ጠይቀዋል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ፣ ወምበራ፣ ድባጢና ቡሌን ወረዳዎች ከባለፈው ሃሙስ ጀምሮ እስከ ዛሬው ማክሰኞ በደረሰ ጥቃት የሰው ህይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎቸ ገለፁ። በዞኑ ጉባ ወረዳ ትናንት ሰኞ በደረሰው ጥቃት ከ 11 ሰዎች ህይወት አልፎአል። በወምበራ ወረዳ በጎንዲ በተባለ ስፋራ ደግሞ ባለፈው ሳምንት ሃሙስ የጸጥታ ሀይሎችን ጨምሮ በግብርና ስራ ላይ የተሰማሩ 16 ሰዎች በዚሁ ጥቃት ሕይወታቸዉን አጥተዋል፤በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች የአካባቢዉ አመልክቷል፡፡ አካባቢዉ ላይ ይኖሩ የነበሩና ጥቃቱ ሲከሰት የደረሱበት ያልታወቀ ሰዎች መኖራቸዉን ተጠቁመዋል፡፡ ከአካባቢው ኮማንድ ፖስት ይህንን ጉዳይ ለማጣራት ያደረግነዉ ጥረት የስልክ ጥሪን ባለመቀበላቸዉ አልተሳካም፡፡

Image may contain: one or more people and outdoor

በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ አልመሽመሽ በተባለ ስፋራ ትናንት ከሰዓት ታጠቂዎቹ በተለያዩ ቦታዎች በመንቀሳቀስ ጉዳት ማድረሳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የግለሰቦችን መኖሪያ ቤቶችንም ማቃጠላቸው የተነገረ ሲሆን የተለያዩ የቁም እንስሳትን መዝረፋቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ጥቃት አድራሾቹ ዛሬ በማንዱራ ወረዳ ጉዳት ማድረሳቸው ታዉቋል።
ከመተከል ዞን ወምበራ ወረዳ ከተማ በ40 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚትገኘዋ በጎንዲ በተበለ ስፋራ ከባለፈው ሃሙስ ጀምሮ የታጡቁ ሸማቂዎች ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን ጉዳት ደረሰባቸው የአካቢው ነዋሪዎች በስልክ ለዶቼቬሌ ገልጸዋል። በዕለቱ ታጠቂዎቹ አድፍጠው በመጠበቅ በጸጥታ ኃይሎች ላይም ጥቃት መፈጸማቸውን ጠቁመዋል። በወምበራ ወረዳ ሰንኮራ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ለሚ ሰንበታ በበጎንዲ የግብርና ስራ ተሰማርተው የነበሩ ሲሆን በስፋራ የደረሰውን ጥቃት ሸሽተው አሁን ከወረዳው ከተማ እነደሚገኙ አመልክቷል።

Image may contain: one or more people, shoes, outdoor and nature

“ታጠቂዎቹ በጎንዲ ላይ ጥቃት ካደረሱ በኃላ ሁለት መኪኖችን አቃጥለዋል። የሞቱት ሰዎች 3ቱ የመነስቡ ቀበሌ ነዋሪዎች ሲሆኑ ሌሎቹ የሰንኮራ፣ ደብረዘይት፣ ጎጆር የተባለ ቀበሌዎች ነዋሪዎች ናቸው። ሁለቱ ደግሞ የአንድ በተሰብ አባላት ሲሆኑ የጸጥታ ሀይሎችም ይገኙበታል። ወደ አስራ ስድስት ሰዎች ህወታቸው አልፈዋልም” ብለዋል።በመተከል ዞን ድባጢ ወረዳ ዳላቲ በተባለ ቦታ ሌላ አደጋኛ ሁኔታ መፈጠሩን ከአካባቢው ዛሬ ከአካባቢዉ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

Image may contain: one or more people, outdoor and nature

ከክልሉ ሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ፣ከዞኑ አስቸካይ ጊዜ አስተዳደደር( ኮማንድ ፖስት) ኃላፊዎች ስለ ጉዳዩ ማብራሪያ ለማግኘት በስልክ ያረኩት ጥረት ስልክ ባለማሳታቸው ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም፡፡ በቅርቡ በዞኑ የተቋቋመው ግብረ ኃይልም በዞኑ ሰላምን ለማስፈን ያስችላሉ የተባሉ ምክክሮችን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ማድረጉን ከኢዜአ ያኘነው መረጃ ያመልክታል፡፡

Image may contain: 1 person, outdoor

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ጨለያ ቀበሌ ዳሊቲ በተባለ ጎጥ በዛሬው ዕለት 27 ሰዎች መገደላቸውን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል።የዓይን እማኙ ግድያው ዛሬ ንጋት በግምት 11 ስዓት ላይ መፈጸሙን፣ጥቃት አድራሾቹ ግድያውን የፈፀሙት በቀስት መሆኑን ከግድያው አምልጠው ከመጡ ዘመዶቻቸው መስማታቸውን ገልጸዋል።
በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች አስከሬን በጨለያ ቀበሌ አስከሬናቸው መሰብሰቡንም ገልፀዋል። ከሟቾቹ በተጨማሪ በርካታ ቁስለኞች በአካባቢው በሚገኝ የጤና ተቋም ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም ተናግረዋል።በርካታ ቁጥር ያላቸው የአጎራባች ቀበሌ ነዋሪዎችም ጥቃቱን በመፍራት ቀያቸውን ለቀው እየሸሹ ነው ብለዋል።
አስከሬናቸው ከተሰበሰቡ 27ቱ ሟቾች ውጭ በአሁኑ ጊዜ በየአካባቢው አስከሬን እየተፈለገ በመሰብሰብ ላይ በመሆኑ የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችልም አስረድተዋል።በአካባቢው እስካሁን የመከላከያ ሰራዊት አለመግባቱንም ጨምረው ገልፀዋል።
ጉዳዩን በተመለከተ የአካባቢውን ባለስልጣናት ጨምሮ የኮማንድ ፖስቱን መሪ ሌትናል ጀነራል አስራት ደነሮን ለማግኘት የእጅ ስልካቸው ላይ ብንደውልም ምላሽ ባለማግኘታችን አስተያየታቸውን ልናካትት አልቻልንም።
በቤንሻንጉል ጉምዝ በመተከል ዞን ካለፈዉ ሳምንት ሐሙስ ጀምሮ ጉባን ፣ወንበራ፣ ድባጤና ቡለን በተባሉ ወረዳዎች ያሸመቁ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢውን ነዋሪዎች ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።