የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።

–
አዲሱ የትራንስ ኢትዮጵያ ኩባንያ ተወካይ ከጅቡቲ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የኩባንያው ንብረት የሆኑ 179 ከባድ ተሽከርካሪዎችን ቁልፎች ተረክበዋል።
–
የኢትዮጵያ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትራንስ ኢትዮጵያ ሽብርተኞችን በገንዘብ በመደገፍ፣ በህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በመሳሪያ የታገዘ ዘረፋ እና ሌሎች ወንጀሎች በመጠርጠሩ ተሸከርካሪዎቹ እንዲመለሱ ትዕዛዝ ሰጥቶ እንደነበር ተገልጿል።
–
በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እና በሚመለከታቸው የጅቡቲ የመንግስት አካላት ትብብር የጅቡቲ መንግሥት ቁልፎቹን ከአሽከርካሪዎቹ መረከብ መቻሉ ተገልጿል።
–
ወደ አገራቸው ለመመለስ ፈቃደኛ ከሆኑት 14 አሽከርካሪዎች በስተቀር ቀሪዎቹ በጅቡቲ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ እንደሚገኙ ተነግሯል።EBC
–