የባልደራስ አመራሮች ይፈቱ !


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ

ለመላው ዴሞክራሲ እና ፍትህ ወዳድ በሙሉ የተላለፈ ጥሪ

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከገባችበት የዘረኝነት አረንቋ ለማውጣትና ከመበታተንም ለመታደግ አለማቀፍና ሀገራዊ ድንጋጌዎችን በማክበር ባለደራስ ፓርቲ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግቆይቷል። ሆኖም ገዥው ፓርቲ መጪውን ምርጫ ከራሱ ጋር ተወዳድሮ ለማሸነፍ እየወሰደ ባለው እርምጃ፣ ለስልጣኔ ይገዳደረኛል በሚላቸው የባልደራስ አመራሮች ላይ ከምርጫ ውድድር ውጪ ለማድረግፍርድ ቤቶችን በአፈናነት እየተጠቀመባቸው ለመሆኑ ተጨባጭ ማስረጃዎችን መዘርዘር ይቻላል፡፡ የባልደራስ ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችን ከዚህ ቀደም የተለያዩ ምክንያቶችን በመደርደር ወከባ እንግልትእና እስር ይፈጸምባቸው እንደነበር ይታወቃል።

በአሁኑ ሰአት በፍርድ ቤት እየተካሄደ ያለው ቧልት ከዚህ ቀደም ይፈጸም ከነበረው ህግን ያለ አግባብበ መጠቀም የማጥቂያ መሳሪያ የማድረግ የተበላሸ አሰራር የቀጠለ ለመሆኑ አየነተኛ ማሳያ ነው። በህግ ሂደቱ እየታየ ያለው በዜጎች መሰረታዊ መብቶች ላይ የሚፈጸም ገደብ የለሽ ቁማር የለውጡ መንግስት ካለፈው ብልሹ አሰራር ትንሽም ቢሆን አለመማሩን አመላካች ነው።

አቶ እስክንድር ነጋ ከእሩብ ክፍለ ዘመን በላይ ለዲሞክራሲ፣ ለፍትህ፣ ለነፃነት እና ለእኩልነት የታገለ መሆኑን እና ከፍተኛ መስዕዋትነት መክፈሉን ዓለም የመሰከረውሃቅ ነው። እንደ አቶ እስክንድር ሁሉ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር (ቀለብ) ስዩም እና አስካለ ደምሌ በሃገራችን ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ባደረጉት ትግል በተለያዩ ወቅቶች ለእስር እና እንግልት መዳረጋቸው ይታወቃል።

አቶ እስክንድር ነጋ፣ስንታየሁ ቸኮል፣አስቴር ስዩም እና አሰካለ ደምሌ የታሰሩት “በአዲስ አበባ ኹከትና ግጭት እንዲፈጠር በመቀስቀስ ተጠርጥረዋል” በሚል ሰንካላ ምክንያት እንደሆነ ይታወሳል።በአሁኑ ሰአት በየአካባቢው ዜጎች ያለ ፍርድ በጠራራ ፀሃይ በአደባባይ እንደ ዕንስሳ በሚታረዱባት ሀገር፣ በአስከፊ ሁኔታ እየተገደሉ ያሉ ንጹሃን ዜጎች ላይ የሚፈጸሙየዘር ማጥፋትን ተቆጣጥሮ ወንጀለኞችን ህግ ፊት ማቅረብ ያልቻለ መንግሥት ፣ህግን የፖለቲካ ተቀናቃኞችን ለማጥቂያነትበማዋል ምንም ጥፋት በሌለባቸው የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራሮችን እስር ቤት በማጎር የፖለቲካ ፍላጎት ማስፈጸሚያነት እየተጠቀመባቸውይገኛል።

በለውጥ ስም ወደ ስልጣን የመጣው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይአህመድ አስተዳደር “ሳይጣራ ሰው አናስርም”እና “መንግስታችን ራሱ ሽብርተኛ ነበር” በሚሉ አማላይ ቃላት የስልጣን ዘመኑን መጀመሩ የአጭር ግዜ ተቀባይነት እንዳስገኘለት አይዘነጋም። ነገር ግን ባልፈጸሙት ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙ የባልደራስ አመራሮች ከአምስት ወር በላይ ፖሊስ “የማጣራው ጉዳይ ስላለ ተጨማሪ ግዜ ይስጠኝ” በማለ በተደጋጋሚ ቀጠሮውን ያለአግባብማራዘሙ እየተፈጸመ ላለው ግፍ ሁነኛማሳያነው።

መጪውን ሀገር አቀፍ ምርጫ አስመልክቶ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት፣ ከየካቲት 8 እስከ የካቲት 21 የዕጩዎች ምዝገባ፣ ከየካቲት 22 እስከ መጋቢት 21 የመራጮች ምዝገባ እንደሚሆን ታውቋል። በአንፃሩ ክሶችን ለማሻሻል የሚሉ ሰንካላ ስበቦችን በመደርደር በተደጋጋሚ ቀጠሮ ተከሳሾችን ሆን ተብሎ በእስር ለማቆየት እየተፈጸመ ያለው ድራማ፣ የባልደራስ አመራሮችን በቅጥፍት ሰበብ ከምርጫው ውድድር ውጭ ለማድረግ እየተካሄደ ያለ ደባ አካል መሆኑን መገመት አይከብድም።

ለሶስት አስርት ዓመታት በስልጣን ላይ የቆየው አምባገነናዊ ስርአት እና አሁን ወደ ስልጣን የመጡ ተተኪዎቻቸው የፍትህ ስርአቱን የተቃዋሚ ወገኖችን ለማጥቂያነት በማዋል ረገድ ተመሳሳይ ተግባር ፈጽመዋል። የአገር ክህደት እና አሸባሪነት የሚሉ የሃሰት ፈጠራ ክሶችን በመደርደር አገዛዙ አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎች የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራሮችን እና አባላትን በመወንጀል የፍትህ ስርዓቱን ለማጥቂያነት በመጠቀም ላይ ይገኛል።

በባልደራስ አመራሮች እና አባላት ላይ እየተፈጸመ ያለው ኢ-ፍትሐዊ አሰራርና አፈና ህገወጥ እና አምባገነኖች የሚታወቁበት የፖለቲካ ተቀናቃኝን የመበቀል ስልት አካል ነው።ኢትዮጵያም የሰብአዊ መብቶችን ለማክበር የገባችውን አለም ዐቀፍ ግዴታ የሚጥስ ሂደት ነው። ስለሆነም ለዴሞክራሲ እና ስብዓዊ መብት የምንቆረቆር ወገኖች አቶ እስክንድርን ጨምሮ ሌሎች የባልደራስ አመራሮች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እንጠይቃለን።

የዴሞክራሲ እና ስብአዊ መብቶች ተቆርቋሪ የሆንን በዓለም ዙሪያ የምንኖ ርሃገር ወዳድ ወገኖች፣ መንግሥት ያለአግባብ ያሰራቸውን የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ እስክንድር ነጋን እና ሌሎች የፓርቲው አመራሮችን እንዲፈታ የሚጠይቅ ዓለም አቀፍ ዘመቻ ለማካሄድ ዝግጅታችንን አጠናቀናል። ስለሆነም ያለአግባብ የተያዙ የህሊና እስረኞችን ለማስፈታት ከዚህ በፊት ሲደረግ ከነበረው ትግል በተለየ እና በተቀናጅ ሁኔታ ውጤታማ የሚያደርጉ የትግል ስልቶችን ነድፈንወደ ተግባርዊ እንቅስቃሴ ገብተናል፡፡

ይህንንም አላማ ከዳር ለማድረስና ለማስፈፀም የተቋቋመው አለም አቀፍ ግብረሀይል ፤ ለመላው ዴሞክራሲ እና ፍትህ ወዳድ በሙሉ የሚሳተፍበት ዘመቻ በመቀላቀል በሚደረገው ርብርብ ይፋ ለምናደርጋቸው የትግል እንቅስቃሴዎች እንደከዚህ ቀደሙ ህዝባችን እራሱን እንዲያዘጋጅ እና ለነፃነት በሚደረገው ትግል ንቁ ተሳታፊ ይሆን ዘንድ በአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ሁሉም የባልደራስ አመራሮች ይፈቱ
ድል ለዴሞክራሲ!!
አለም አቀፍ ግብረሀይል