የአ/አበባ ሀ/ስብከት እንዘጭ እንቦጭ! በመዝባሪነቱ የተነሣው ኤልያስ ተጫነ ለ3ኛ ጊዜ በሒሳብና በጀት ሓላፊነት ተመደበ፤ ለውጥ ፈላጊዎች ሁሉ ሊቃወሙት ይገባል

ባለፈው ሰኞ ከተመደቡት 14 የዋና ክፍል ሓላፊዎች አንዱ ነው፤ የሒሳብና በጀት አሠራሩ፣ የሀ/ስብከቱ ለውጥ ዋነኛ ማሳያ ነበር፤ ለውጡን የማያሳካ፣ ግልጽነትና አርኣያነት የጎደለው ምደባ ነው፤ ከጉድና ጉደኞች እንዳይወጣና እንዳይለወጥ የተረገመ መስሏል፤ ††† አጥቢያዎችን፣ የ112 ሚሊዮን ብር የፈሰስ ባለዕዳ ያደረገ ነው፤ ደመወዝ ለማጸደቅ የወር ጭማሪውን በጉቦኝነት ሲበላ ኖሯል፤ የዘመናዊ ቤቶችና ፎቅ፣የባንክ አክስዮንና ግሮሰሪ ባለቤት ነው፤ ለውጥ ፈላጊ …