የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ዐቢይ ኮሚቴ: ለሶማሌ ሀ/ስብከት ተጎጅዎች የመጀመሪያ አስቸኳይ ርዳታ ነገ ያደርሳል፤ ምእመናኑን ያጽናናል፤ ጉዳቱን ያጠናል

ዐቢይ ኮሚቴው፣ በሦስት ንኡሳን ኮሚቴዎች ተዋቅሯል፤ የዘላቂ ድጋፍ የገንዘብ ርዳታ የሚሰበሰብበት አካውንት በንግድ ባንክ ከፍቷል፤ አህጉረ ስብከት፣ ግለሰቦች፣ መንግሥታዊ የኾኑና ያልኾኑ አካላት እንዲተባበሩ ጠየቀ፤ ††† የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000254922898 አራት ኪሎ ቅርንጫፍ ††† በኢትዮጵያ ሶማሌ ሀገረ ስብከት፣ በጅግጅጋና የአካባቢው ዞኖች፣ በተፈጸመው አሠቃቂ ግድያና የንብረት ውድመት ጉዳት ለደረሰባቸው ካህናት፣ ምእመናንና አብያተ ክርስቲያን፣ ድጋፍ የሚያደርግና ርዳታ የሚያሰባብስብ …