ግድያው በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ አሁንም እንዳልቆመ ተሰምቷል


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


(አብመድ) – ግድያው አሁንም እንዳልቆመ በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ተናገሩ:: በመተከል ዞን ከግድያ የተረፉ ዜጎችን የፌዴራል ፖሊስ በጸጥታ ጉዳይ ላይ እንዳወያያቸው ተፈናቃዮች ገልጸዋል፡፡
በወይይቱም በግድያው ምክንያት ትተውት የመጡት ሃብት እና ንብረት የተዘረፈ በመሆኑ ችግር ላይ መውደቃቸውንና አሁንም የሰው ህይወት እየጠፋ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከነበሩበት ቀበሌ መፈናቀላቸውንና ቤት ንብረታቸው መውደሙን በውይይቱ እንዳነሱ ለአብመድ በስልክ ገልጸዋል።
አሁን ላይ ችግር ላይ መውደቃቸውን የተናገሩት ተፈናቃዮቹ የጸጥታው ጉዳይ መፍትሄ የሚያገኝ ከሆነ በጊዜያዊ መጠለያ ቢሆን ወደ ቀያቸው ተመልሰው የመኖር ፍላጎት እንዳላቸው ነው የገለጹት፡፡
የጥቃቱን አለመቆምና ለተፈናቃዮች እየተደረገላቸው ያለውን ድጋፍ ለመጠየቅ ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም ግንባታና ደህንነት ቢሮ እንዲሁም የምግብ ዋስትና እና አደጋ መከላከል ጽህፈት ቤት የስራ ኃላፊዎች በተደጋጋሚ ስልክ ብንደውልም ሊያነሱ አልቻሉም፡፡