ሕወሓት የሠሜን ዕዝ ም/አዛዥ ብ/ጄ አዳምነህ መንግስቴን ከመኖሪያ ቤቱ አፍና ወስዳለች


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ

የሠሜን ዕዝ ም/አዛዥ ብ/ጄ አዳምነህ መንግስቴን ከመኖሪያ ቤቱ እንዲሁም ሌሎችንም መሪዎች አፍና ወስዳለች፡፡

ዘሪሁን ገሠሠትህነግ መቀሌ አካባቢ የሚገኘውን አዋሽ ካምፕ ፥ የመከላከያ ዲፖ ፥ ኩዊሃ የሚገኘው 4ተኛ ሜካናይዝድ ክፍለጦር ፣ አንዳንድ ማዘዣ ጣቢያና ካምፖችን ….ወዘተ ተቆጣጥራ በከፈተችው ድንገተኛ ጥቃት በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ ጉዳት አድራሳ ነበር፡፡ 4ተኛ ሜካናይዝድን ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ ዘርፋለች፡፡

አራተኛ ሚካናይዝድ ይመራ የነበረው የመቀሌ አካባቢ ነዋሪና ተወላጅ በነበረ የክፍለ ጦር አዛዥ የነበረ ሲሆን አብይ በእንዝላልነት እስካሁን አቆይቶት የዛሬ ወር ገደማ ነው የተነሳው! ነገርግን ሠራዊቱ በአሁኑ ሰአት የለቀቃቸውን ቦታዎች መልሶ ተቆጣጥሮ የከበባ ስራ ብቻ እየሠራ ይገኛል፡፡ ከዚያ በተረፈ አየር ድብደባም የተፈፀመው ከታርጌት ውጭ ለማስፈራሪያ የተደረገ እንጂ ሌላ ነገር አይደለም፡፡

ህወሓት ግን በአየር ተደበደብኩ ብላ ለፕሮፓጋንዳ ተጠቀመችበት! አዛዦቹን የሚመታ ትጥቅ አለኝ ምናምን የምትለው ግን ተራ ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡

 በርግጥ ባልተጠበቀ ሁኔታ በከፈተችው ጥቃት ብዙ ሠው ገድላለች ፤ ዘርፋለች ፤ እንዲሁም የሠሜን ዕዝ ም/አዛዥ ብ/ጄ አዳምነህ መንግስቴን ከመኖሪያ ቤቱ እንዲሁም ሌሎችንም መሪዎች አፍና ወስዳለች፡፡
መንግሥት እየዞረ እጅ ስጡ ከማለት ባለፈ ቦታዎቹን ከተቆጣጠረ በኃላ አንድ ጥይት አልተኮሰም፡፡ ምናልባት በቀጣይ ቀናት ውጊያ ሊከፈት ይችል ይሆን ይሆናል፡፡ ውጊያ ያለውም በምዕራብ በኩል ያለው ከአማራ ልዩ ሀይልና ፏኖ ጋር ብቻ ነው፡፡ የተወሠነ መከላከያም ተሳትፏል፡፡
በተረፈ ዝም ብላችሁ ሀገር ምድሩን በሠበር ዜና ከምትቀውጡት በምእራብ በኩል ያለውን ሀይል አቅሙን እንዳይጨርስ በስልት እንዲጓዝ አሳውቁ::