ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ዙርያ የግብፅን አቋም እንድትቀበል ለማድረግ ያሰበ ነው፣ ይህም ስሜት የማይሰጥ ነው – ኸርማን ኮህን


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አምባሳደር ኸርማን ኮህን አሜሪካ ለኢትዮጵያ ከምትሰጠው ድጋፍ ውስጥ ከፊሉን ለመቁረጥ መወሰኗን ተችተዋል!
እ.አ.አ ከ1989 እስከ 1991 የአሜሪካ አፍሪካ ጉዳዮች ሀላፊ የነበሩት ኮህን ድርጊቱ “ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ዙርያ የግብፅን አቋም እንድትቀበል ለማድረግ ያሰበ ነው፣ ይህም ስሜት የማይሰጥ ነው” ብለዋል።

ዲፕሎማቱ አክለውም ይህ የአሜሪካ አካሄድ ከወገኝትነት የፀዳ ሸምጋይ መሆኗን ጥያቄ ውስጥ የሚከት እንዲሁም ኢትዮጵያ በአቋሟ ግትር እንድትሆን ያደርጋል ብለዋል።
ከዚህ በፊትም አሜሪካዊው የመብት ተሟጋች ጄሲ ጃክሰን እንዲሁም ስድስት የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት የአሜሪካንን ውሳኔ በመቃወም ደብዳቤ ለስቴት ዲፓርትመንት ፅፈዋል።