የሐይማኖት ተቋማትና የመንግስት ፖሊሲዎች ለትውልዱ መላሸቅ ተጠያቂዎች ናቸው – ኃላፊነትም ሊወስዱ ይገባል።


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።

የሐይማኖት ተቋማትና የመንግስት ፖሊሲዎች ለትውልዱ መላሸቅ ተጠያቂዎች ናቸው። ኃላፊነትም ሊወስዱ ይገባል።

ምንሊክ ሳልሳዊ – የሐይማኖት አስተማሪዎችና የመንግስት ፖሊሲዎች ትውልድን በመቅረጽ ረገድ ግዴታ አለባቸው። ግዴታቸውን የማያውቁ የሐይማኖት ተቋማትና የፖሊሲ አውጪዎችና አስፈፃሚዎች ወንጀለኞች ናቸው። ኢሕአዴግ ስሙን ከመቀየር ጀምሮ የተወሰኑ የለውጥ ሂደቶችን በተግባር ከማሳየቱ ውጪ መንግስታዊ መዋቅሮችም ይሁኑ ፖሊሲዎች አለወጠም። ከመለስ ዜናዊ ሲወርድ ሲዋረድ በመጣው የዘር ፖለቲካ ፖሊሲና የዳሸቀ የትምሕርት ፖሊሲ ወጣቱን የሞት ዲቃላ እንዲሆን አድርጎታል።ለዚህም ገዢው ፓርቲ ለወጣቱ በጥፋት ኃይሎች መታለል ኋላፊነቱን ሊወስድ ይገባል። መንግስት የደኸዩ ፖሊሲዎቹና ብቃት የሌላቸው የፖሊሲ አስፈጻሚዎችን ታቅፎ ተቀምጦ ስር ነቀል የመዋቅር ማሻሻያ አለማድረጉ ተጨምሮበት ተደራራቢ አደጋዎችን እያስተናገደ ነው።

የሃይማኖት ተቋማት ወጣቱን ቅን አሳቢ፤ ለወገንና ለሐገር ተቆርቋሪ፣ በፈጣሪው ተስፋ የሚያደርግ፣ መረጋጋትን የተላበሰ አስተዋይ ክብርንና ፍቅርን የመሳሰሉን እንዲያውቅ እንዲሆንና እንዲመራበት አድርገው በሐይማኖታዊ ቀኖናቸው ባለመቅረፃቸው ለሚደርሱት ጥፋቶች ኃላፊነቱን ሊወስዱ ይገባል።በርካታ ቤተክርስቲያናት፣ በርካታ መስጂዶች፣ በርካታ የፕሮቴስታት አደራሾች በተገነቡበት፣ በርካታ ቀሳውስት፣ በርካታ ኡስታዞች፣ በርካታ ፓስተሮችና ነቢይ ነን ባዮች እንዲሆም በየስርቻው የተወሸቁ የሃይማኖት አስተማሪ ነን ባዮች በፈሉባት አገር ላይ ወጣቱ ሞራሉ በፈጣሪ ፍርሐት እንዳይታነጽ ሆኖ በግድያና በንብረት ማውደም ላይ ሲሰማራ ማየት የሃይማኖት ተቋማት የሞራል ልእልና መሞቱን ይመሰክራል።

በሐገሪቱ በማይረባ የትምሕርት ፖሊሲ የተደቆሰውን ወጣት ኃይል በተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ እንዲኖር በስራ ማጣት እንዲሰቃይ የሚያደርጉ የመንግስት የዘር ፖለቲካና የትምሕርት ፖሊሲዎች ሊወገዱ ይገባል። የሃይማኖት ተቋማትም ሕዝብን እያጭበረበሩ ገንዘብ ከመሰብሰብና የራስን ዝና ከመገንባት ወጥተው ወጣቱ በአፋጣኝ በግብረገብነት ሊቀርፁ ይገባል።ምንሊክ ሳልሳዊ