እስክንድር ነጋን ጨምሮ የባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች ከመኖሪያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች እርዳታ ሲሰጡ ታሠሩ

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) የኮሮና ተህዋሲ እያደረሰ ያለውን ምጣኔ ኃብታዊ ጫና ምክንያት በማድረግ ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የምግብ እህል ለማከፋፈል እየተንቀሳቀሰ ባለበት ወቅት አመራሮቹና አባላቱ ታስረዋል፡፡
ፖሊስ አመራሮች ያሰረው “ከላይ በመጣ ትዕዛዝ” መሆኑን የገለጸ ሲሆን፣ እርዳታውንም ተይዟል። የፓርቲውን ፕሬዚደንት እስክንድር ነጋን ጨምሮ ከ15 በላይ አመራሮችና አባላት በአሁኑ ጊዜ በኮልፌ ቀራኒዮ፤ ካራ ቆሬ ፖሊስ ጣቢያ ታስረዋል፡፡
የእርዳት እህል ጭነው የነበሩት ሁለት አይሱዙ ተሸከርካሪዎችም ከነጭነታቸው በፖሊስ ተወስደዋል፡፡
ጠበቃዎችና ሌሎች አመራሮች ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ፖሊስ ጣቢያው አምርተዋል፡፡