የመቐለ ፖሊስ አንድ ወጣት በመግደል ሁለት ወጣቶችን ማቁሰሉ ተሰማ

መረጃ ቲቪን ሰብስክራይብ በማድረግ ወቅታዊ ዜናዎችን፣ ትንተናዎችን፣ የኪነጥበብ ፕሮግራሞችን እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ማግኘት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

የዓረና ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት የሆነው ዓምዶም ገብረስላሴ በማሕበራዊ ድረገጽ በለቀቀው መረጃ እንደገለጸውየመቐለ ፖሊስ በውጣቶች ላይ ተኩሶ ኣንድ ወጣት በመግደል ሁለት ወጣቶች በከባድ እንዲቆስሉ ኣድርገዋል።

ትናንት 09/09/2012 ዓ/ም በመቐለ 05 ቀበሌ ኑዋሪ በሆኑት ወጣቶች ተኩስ በመክፈት ሽሻይ የተባለ ኣንድ ወጣት ወድያውኑ ሂወቱ ሲያልፍ ጠዓመ ሓድጉና ሞገስ ሓዱሽ የተባሉት ሁለት ወጣቶች ደግሞ ክፉኛ ቆስለው ዓይደር ሆስፒታል ለህክምና ገብተዋል።

ለግድያው ምክንያት የተባለው “ኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የወጣው ስቸኳይ ግዜ ኣዋጅ በመጣስ ተሰብስባቹሃል” የሚል ሲሆን ፖሊስ “ተበተኑ” በማለት ወጣት ሽሻይን ተኩሶ እንደገደለው ተገልፀዋል።

ቶኩሱ ለሰዓታት የቆየ በመሆኑ የ03፣ 05፣ 06 ቀበሌ በርካታ ህዝብ፣ ወጣቶችና ከፍተኛ ቁጣና ተቀስቅሰዋል።

እንዲሁም መንግስት ችግሩ ለማረጋጋት በርካታ ፖሊስ፣ ምልሻ፣ ኣድማ በታኝ ልዩ ሃይል ፖሊሶች ልኮ ለመረጋጋት ጥረት ኣድርገዋል።

ፖሊስ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በታወጀው ኣስቸኳይ ግዜ ኣዋጅ ምክንያት ሰው በጥይት ሲገድል ለሁለተኛ ግዜው ነው።

ከኣዋጁ በኋላ በጥይት ተኩሶ የኣካል ጉዳት ማድረስ፣ ደብድቦ ኣካል ማጉደል፣ ያለምክንያት ማሰር፣ ሌሎች ጥፋቶች በፖሊስ እየተፈፀሙ ይገኛሉ።