መንግስት የአምስት ወራት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊያውጅ ይችላል ተባለ ።
መንግስት የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የአምስት ወራት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊያውጅ ይችላል ተባለ ። ሰሞኑን ከፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ጋር ሲመክሩ የሰነበቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከፓርቲያቸውን አመራሮች ስብሰባ ተቀምጠዋል። የምክክሩና የስብሰባው ዋናው ዓላማ በቀጣይነት በሕገመንግስቱ ምእራፍ 11 አንቀፅ 93 ንዑስ አንቀጽ 1/ሀ መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ መሆኑ ተሰምቷል። ሰሞኑን ከፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ጋር የተገናኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥልቀት የተወያዩት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዙሪያ መሆኑ መረጃዎች ጠቁመዋል።የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎም ሃገራዊ ምርጫውን የማራዘም ሀሳብም አለው ተብሏል፡፡ #MinilikSalsawi