“እጅ ይሰጣሉ ያላችኋቸው የፋኖ አመራሮች እስካሁን ለምን አልሰጡም?” የተሐድሶ ኮሚሽኑ!
ከብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን፡ በምክትል ኮሚሽነሩ ብርጋዲየር ጄነራል ደርቤ መኩሪያ የተፈረመ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ለነ ማስረሻ ሰጤ ተሰቷቸዋል።
ደብዳቤው “እጅ ይሰጣሉ ያላችኋቸው የፋኖ አመራሮች እስካሁን ለምን አልሰጡም?” የሚል ነው።
የተሐድሶ ኮሚሽኑ “እጅ የሚሰጡ የፋኖ አመራሮችንና አባሎችን በኤግዚቢሽን መልክ ለማስጎብኘት በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች እቅድ መያዙን ገልፆ፡ “በአጭር ቀናት ውስጥ እንዲመጡ አስደርጉ” ሲል ቀጭን ትዕዛዝ ሰጥቷቸዋል።
በሆዳቸው ወድቀው የሕልውና ትግሉንና ታላቁን የአማራ ሕዝብን የካዱት ባንዳዎቹ እነ ማስረሻ ሰጤና መስፍንም፡ በጭንቀት ተሞልተው “እባካችሁ ትንሽ ታገሱን” በሚል በር በሩን እያዩ ቢሆንም ነገር ግን እስካሁን ዝር ያለ ነገር የለም።