እንግሊዝ ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ማዘጋጀቷን አስታወቀች።

ጠቅላይ ሚኒስትሯ በኮሮና ቫይረስ የተጠቃባት እንግሊዝ ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ማዘጋጀቷን አስታወቀች።
የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪሰ ጆንሰን በኮቪድ 19 መያዛቸዉን ተከትሎ ሕመማቸው በመባባሱ ትናንት ምሽት ወደ ጽኑ ሕክምና ክትትል መግባታቸው ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕመማቸው ቢጸና ወይም ሌላ የከፋ ችግር ቢገጥማቸዉ በሚል ዶሚኒክ ራብ በተጠባባቂነት መመረጣቸዉ ታዉቋል፡፡
የአገሪቱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን እያገለገሉ የሚገኙት ዶሚኒክ ራብ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን መምራት የማይችሉ ደረጃ ላይ ከደረሱ እንደሚተኳቸዉም ሮይተርስ አስነብቧል፡፡
በአሁኑ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በፅኑ ህሙማን ክፍል እንደሚገኙ የተገለፀ ሲሆን እንግሊዝ ግን አሁንም ድረስ በእርሳቸዉ ነዉ የምትመራዉ፡፡
የ46 አመቱ ዶሚኒክ ራብ እንግሊዝ ከአዉሮፓ ህብረት መዉጣት የለብትም በሚል የቦሪስን ሃሳብ ሲቃወሙ እንደነበረም ተነግሯል፡፡
ራብ እ.ኤ .አ በ2010 ወደ ፓርላማ ከመገባታቸዉ በፊት በተለያዩ የዲፕሎማሲ ስራዎች ላይ አገራቸዉን አገልግለዋል፡፡
EThio FM