ከልብ የተሰማኝን ምስጋናዬን አቀርባለዉ – ጠ/ሚ አብይ አህመድ

መረጃ ቲቪን ሰብስክራይብ በማድረግ ወቅታዊ ዜናዎችን፣ ትንተናዎችን፣ የኪነጥበብ ፕሮግራሞችን እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ማግኘት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

Imageከልብ የተሰማኝን ምስጋናዬን አቀርባለዉ  – ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ 
የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የቀረበውን ጥሪ በመቀበል ምላሽ ለሰጡ ወገኖች ምስጋና ቀረበ
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ያቀረበውን ጥሪ ተቀብለው ባለፉት ቀናት ደግነት እና ልግስናቸውን ያሳዩ ኢትዮጵያውያንን አመስግነዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመቶ ኩንታል የሚበልጥ ጤፍ ከለገሱት አርሶ አደር ጀምሮ፤የንግድ ሕንጻዎቻቸውን እና ቤቶቻቸውን ለይቶ ለመከታተያ እንዲሆን ያቀረቡ ነጋዴዎች እና ባለሐብቶች ፤መኪኖቻቸውን ለግልጋሎት ያመጡ ግለሰቦች፤ብዛት ያለውን የምግብ ድጋፍ ያደረጉ ንቁ ወጣቶች ተሳትፏቸውን በተግባር አሳይተዋል ነው ያሉት፡፡
በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ የተለገሰው የደግነት ስራ፤ብርታት እንዲሁም አዎንታዊ እና ገንቢ ተሳትፎ የሚመሰገን መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በትዊተር ገፃቸው ላይ ገልፀዋል፡፡