በኮሮና ቫይረስ ተይዘዉ ካገገሙ ህሙማን ድጋሚ ሲመረመሩ ቫይረሱ ስለተገኘባቸው የጤና ባለሙያዎችን አስደንግጧል።

በቻይና በኮሮና ቫይረስ ተይዘዉ ካገገሙ ህሙማን 14 በመቶ የሚሆኑት ድጋሚ ሲመረመሩ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡
የሃገሪቱ የጤና ባለሙያዎች እንዳሉት ቀደም ሲል በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው አገግመዉ በወጡ ታማሚዎች ላይ ምርመራ ሲደረግ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡ይህም የጤና ባለሙያዎችን አስደንግጧል፡፡
ባለሙያዎቹ እንዳሉት በቫይረሱ ተይዘዉ ከዉጭ በሚገቡና ቫይረሱ በሰዎች ላይ ምንም አይነት ምልክት ሳያሳይ በመቆየት በሀገሪቱ ለሁለተኛ ጊዜ ወረርሽኙ ሊቀሰቀስ እንደሚችል ስጋታቸዉን እየገለጹ ነዉ፡፡
በዚህም በመጀመሪያ ወረርሽኙ የተቀሰቀሰባት የሁቤ ግዛት ነዋሪዎች የእንቅስቃሴ ገደቡ መነሳቱን ተከትሎ በስጋት አካባቢዉን ለቀዉ ወደ ሌላ ቦታ እየተሰደዱ መሆኑን ዴይሉ ሜይል በሰበር ዜና ዘግቧል፡፡
የጤና ባለሙያዎች ባደረጉት ምርመራ ከ147 ሰዎች ዉስጥ 5ቱ በድጋሚ ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነዉ ተገኝተዋል ብለዋል፡፡
በጣም አስደንጋጩ ጉዳይ ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ለቫይረሱ የተጋለጡ ሰዎች ምንም አይነት የህመም ምልክት እያሳዩ አይደለም ነዉ የተባለዉ፡፡
ሰዎች አሁንም ቢሆን በቫይረሱ ተይዘዉ ካገገሙ ሰዎች ጋር አካላዊ ፈቀቅታን ማድረግ እንዳለባቸዉም መክረዋል፡፡
ባለሙያዎቹ በዚህ ጉዳይ ላይ ሁለት አይነት አስተያየቶችን እየሰጡ ሲሆን ሰዎቹ ቀድሞም ነጻ የተባሉት በምርመራ ስህተት ነበር ሲሉ፤ገሚሶቹ ደግሞ አይደለም በድጋሚ ነዉ የተጋለጡት በሚል ሃሳብ ያቀርባሉ፡፡
በድጋሚ የተጋለጡት ግን ከሌሎች ተላልፎባቸዉ ይሁን የራሳቸዉ የቀደመ ህመም አገርሽቶ የሚለዉን ጉዳይ ለመለየት አሁንም አስቸጋሪ መሆኑን ባለሙያዎቹ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8