ሕዝቡ ቢመከርም አንዱ ከሌላዉ ጋር የሚደርገዉን የቅርብ ግንኙነት አላቋረጠም ተባለ

መረጃ ቲቪን ሰብስክራይብ በማድረግ ወቅታዊ ዜናዎችን፣ ትንተናዎችን፣ የኪነጥበብ ፕሮግራሞችን እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ማግኘት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

DW : የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሮና ተሕዋሲን ለመከላከልና በተለያዩ እርምጃዎች የሚጎዳዉን ሕዝብ ለመደጎም የነደፈው ስልት ካለ ይፋ እንዲያደረግ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችና አንድ ባለሙያ ጠየቁ።ሕዝቡ እንዲጠነቀቅ መንግስትና ሐኪሞች በተደጋጋሚ ቢመክሩም፣ ሰዉ አንዱ ከሌላዉ ጋር የሚደርገዉን የቅርብ ግንኙነት አላቋረጠም።አንዱ ከሌላዉ እንዲራራቅ የሚሰጡ ምክሮችና ማስጠንቀቂያዎችን ገሚሱ ችላ ሲለዉ፣ የተቀረዉ ደግሞ በኑሮ አስገዳጅነት ገቢር ማድረግ አልቻለም። የሕዝቡ የአኗኗር ልማድ እንዲሁም የኑሮ ደረጃ የፈጠረው ከመገናኘት ያለመቆጠብ አዝማሚያ ለችግር መባባስ የበለጠ ሰበብ ከመሆኑ በፊት ዘዴ እንዲፈለግለት የአዲስ አበባዉ ዘጋቢያችን ሰለሞን ሙጬ ያነጋገርናቸው የከተማይቱ ነዋሪዎች ጠይቀዋል።