በአዲስ አበባ 300 ሺህ ያህል የመንግስት ሰራተኞች በቤታቸው እንደሚሰሩ ታውቋል


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።

በቤታቸው ውስጥ ሆነው ይስሩ የተባሉት የፌደራል መስሪያ ቤት ሰራተኞች 300 ሺህ ያህል መሆናቸውን የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በተለይም ለዶቼ ቬለ ገለጸ።
ሰራተኛቹ የኮሮና ተኅዋሲን ስርጭት ለመግታት የሚረዳውን ማህበራዊ መራራቅ ከተል ስላላባቸው ነው ትናንት ባሚኒስትሮች ምክር ቤት በቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ የተወሰነው።

ምን ያህሉ ሰራተኛ እና የትኞቹ ሰራተኞች አገልግሎት እየሰጡ ይቆዩ የሚለው በእያንዳንዱ መስሪያ ቤት የስራ ጠባይ እንደሚወሰንም ታውቋል።
በዚሁ መሰረት አብዛኞቹ መስሪያ ቤቶች ክህንን ተግባራዊ እንዳደረጉት የፌዴራን ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር በዛብህ ገ / እየሱስ ተናግረዋል።
በአማካይ ሰላሳ በመቶ ያህሉ ሰራተኞች በየ መስሪያ ቤቱ አገልግሎት ቢሰጡ ቀሪዎቹ በቤታቸው ይውላሉም ብለዋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አለም አቀፍ ግንኙነት፣ ትብብርና ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዳይሬክተሩ ዶክተር ደመቀ አጭሶ ውሳኔው ጥቅል ፖሊሲ መሆኑን አመልክተው እንደ ባንክ፣ መብራት ሃይል ፣ ወሳኝ ኩነት የመሳሰሉ መስሪያ ቤቶችን የማይመለከት መሆኑ ተገቢ ነው ብለዋል።
ሰራተኛቹ በቤታቸው ይስሩ ሲባል ግን አስቻይ ሁኔታ የፈጠሩ መስሪያ ቤቶችን እንጅ ሁሉንም ማለት እንዳልሆነ ገልጸዋል።
የግድ ሁሉም በቤቱ ውስጥ ይሰራል ማለት እንዳልሆነም እምነታቸው መሆኑን ተናግረዋል።

የኢንተርኔት ግልጋሎት ምቹ ሁኔታ ያለበት መስሪያ ቤት ውስጥ የምትሰራ ሰራተኛ ለ ዶቼ ቬለ የዛሬ ውሎዋን ስትናገር ፣ ከ ሶስት እስከ እምስት ሰአት በየቤታቸው ካሉ ባልደረቦቿ ጋር ለስብሰባ ተቀምጣ መደበኛ ስራዋን ስታከናውን ውላለች።
በሌላ በኩል ፋይናንስ ክፍል ውስጥ የሚሰራ የሌላ መስሪያ ቤት ሰራተኛ የደመዎዝ እና ሌሎች ጉዳይ ስራዎች እዚያው ቢሮ ውስጥ መከወን ስላለበት ስራውን ቢሮው ውስጥ ሆኖ እንደሌላው ጊዜ ሲያከናውን መዋሉንና ፣ ቤታቸው ፍንዲሆኑ የተወሰነው ሰራተኞች ዝርዝር በግልጽ ተጽፎ በማስታወቂያ መመልከቱንም ተናግሯል።