" /> በአማራ ክልል የሚከናወኑ ስብሰባዎች ከዛሬ ጀምሮ ታግደዋል | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

በአማራ ክልል የሚከናወኑ ስብሰባዎች ከዛሬ ጀምሮ ታግደዋል

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በአማራ ክልል ከዛሬ ጀምሮ ምንም ዓይነት ስብሰባዎች እንደማይካሄዱ ተገልጿል።
በክልሉ ከዛሬ ጀምሮ በጸጥታ ጉዳይ በጥንቃቄ ከሚከናወኑ ምክክሮች ውጭ ምንም ዓይነት ስብሰባ እንደማይካሄድ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ፈንታ ማንደፍሮ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
በተጨማሪም በክልሉ የሚገኙ የመጠጥ እና ጭፈራ ቤቶች ላልተወሰነ ጊዜ ሙሉ በሙሉ እንዲዘጉ ተወስኗል።
የክልሉን ህዝብ ህልውና የሚፈታተኑ የጸጥታና ጤና-ነክ ውይይቶች እንደየአስፈላጊነቱ ቁጥራቸው ከ15 ባልበለጡ ሰዎች በየቀኑም ቢሆን በጥንቃቄ ሊከናወኑ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።
ከዚህ ባለፈ ከዛሬ ጀምሮ የከተማ ታክሲዎች ስምንት ሰዎችን፣ ባለ ሦሰት እግር ባጃጅ ደግሞ ሁለት ሰዎችን ብቻ እንዲያጓጉዙ መወሰኑን ገልጸዋል።
ይህን ህግ ተላልፎ በሚገኝ ማንኛውም አካል ላይ ተገቢው እርምጃ እንደሚወስድ እና በርዕሰ መስተዳደሩ የሚመራው ኮማንድ ፖስትም ተዘዋውሮ ምልከታ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
ምንጭ፡- ኢዜአ

የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV