" /> ስኳርና ኬሚካል ከቀይ አፈር ጋር በመቀላቀል ማር ነው ብሎ ለመሸጥ ሲያዘጋጅ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

ስኳርና ኬሚካል ከቀይ አፈር ጋር በመቀላቀል ማር ነው ብሎ ለመሸጥ ሲያዘጋጅ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

ስኳርና ኬሚካል ከቀይ አፈር ጋር በመቀላቀል ማር ነው ብሎ ለመሸጥ ሲያዘጋጅ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ስኳር እና ኬሚካል ከቀይ አፈር ጋር በመቀላቀል ማር ነው ብሎ ለመሸጥ ሲያዘጋጅ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
ግለሰቡ ሙሉ መኖሪያ ግቢ ተከራይቶ ህገ – ወጥ ተግባሩን ሲፈፅም በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው ፖሊስ በጥርጣሬ ባደረገው ማጣራት ነው።
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል።
ግለሰቡ መርካቶን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ማር ነው ብሎ ያዘጋጀውን ባዕድ ነገር ሲሸጥ እንደቆየ ተገልጿል።
በተጨማሪም ከኮሮና ቫይረስ ወረርሸኝ ጋር ተያይዞ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት በሚፈፅሙ እና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ቁጥጥሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም የክፍለ ከተማው የወረዳ 11 ንግድና ኢንዱስትሪ ፅህፈት ቤት ሃላፊ መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV