" /> መንገደኞች በሆቴል ውስጥ ተለይተው ለ14 ቀናት እንዲያቆዩ የሚያስገድደው ውሳኔ ተግባራዊ መሆን ጀመረ | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

መንገደኞች በሆቴል ውስጥ ተለይተው ለ14 ቀናት እንዲያቆዩ የሚያስገድደው ውሳኔ ተግባራዊ መሆን ጀመረ

መንገደኞች በሆቴል ውስጥ ተለይተው ለ14 ቀናት እንዲያቆዩ የሚያስገድደው ውሳኔ ተግባራዊ መሆን ጀመረ

መንግሥት አርብ ዕለት ይፋ ባደረገው ውሳኔ መሰረት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ማናቸውም መንገደኞች ለ14 ቀናት ወደ በለይቶ ማቆያ እንዲገቡ የሚደረገው ከዕከለ ሌሊት ጀምሮ ወደ ተግባር መለወጡ ተሰምቷል።

በመሆኑም ከትላንት ዕሁድ እኩለ ሌሊት ጀምሮ የሚገቡ ሁሉም መንገደኞች በስካይ ላይት ወይም በጊዮን ሆቴል ለ14 ቀናት በራሳቸው ወጪ ተለይተው ይቆያሉ ተብሏል።

እንዲሁም ዲፕሎማቶች አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ በየአገራቸው ኤምባሲዎች እራሳቸውን ለ14 ቀናት ለይተው ይቆያሉ።

የትራንዚት በረራ መንገደኞችም የትራንዚት በረራቸውን እስኪያገኙ ድረስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት በሆነው በስካይ ላይት ሆቴል ተለይተው ይቆያሉ።


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV