የካራ ማራ ድል 42ኛ ዓመት – የካራማራን ድል ስናነሳ ጄኔራል ካሳዬ ጨመዳን አንዘነጋም ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የሶማሊያው መሪ ዚያድ ባሬ ” ታላቋ ሶማሊያ”ን እመሰርታለሁ በሚል ቅዠት ኢትዮጵያን በመውረሩ ህዝቡ ለሀገሩ ዳር ድንበር ዘብ እንዲቆም ጓድ ሊቀመንበር መንግሥቱ ኃ/ማርያም ሚያዝያ 4 ቀን 1969 ዓ.ም በቴሌቭዥን መስኮት ቀርበው ጥሪ አስተላለፉ።

“… ታፍራና ተከብራ የኖረችው ኢትዮጵያ ተደፍራለች። … ለብዙ ሺህ አመታት አስከብሮን የኖረው አኩሪ ታሪካችን በዚህ አብዮታዊ አዲስ ትውልድ ጊዜ መጉደፍ የለበትም። አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያዊት! የኢትዮጵያ ሕዝብ! ለክብርህንና ነፃነትህን ለመድፈር አገርህን ለመቁረስ የተጀመረው ጣልቃ ገብነትና ወረራ ከመለዮ ለባሹ ጋር ተሰልፈህ ለመደምሰስ የምትዘጋጅበት ጊዜ አሁን ነው። ተነስ! ታጠቅ! እናሸንፋለን!”

ከዚህ ጥሪ በኋላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዳር እስከ ዳር ገንፍሎ ተነስቶ በ3 ወር ግዜ ውስጥ ታጠቅ ተብሎ በተሰየመው ማሰልጠኛ ቦታ ሰልጥኖ ከኩባ፣ በሶቪየት ሕብረት እና ምስራቅ ጀርመን አንዲሁም የመን ጋር በጋራ በመሆን ትልቁን የካራ ማራ ድል የተጎናፀፉ።

የካራማራን ድል ስናነሳ ብሄራዊ ጀግናችንን ጄኔራል ካሳዬ ጨመዳን አንዘነጋም ።

Image may contain: 1 person, textከምሥራቅ ጦር ግምባር ጀምሮ ኤርትራ ከምፅዋ እስከ ከረን፤ ናቅፋ ድረስ በስፋት የሚወራላቸው ብርጋዲየር ጄኔራል ካሳዬ ጨመዳ በካራማራ ጦርነት ባደረጉት ታላቅ ጀብዱ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጀግና ሜዳይ ተሸላሚ ናቸው ።

በሰራዊቱ ዘንድ ባላቸው ተቀባይነት በተለይም እርሳቸው የሚመሯቸው የ16ኛ ሰንጥቅ ሜካናይዝድ ብርጌድ አባሎች ጄኔራል ካሳዬ ጨመዳን በአመራራቸው ስኬት ከመውደዳቸው የተነሳ ” ካሣዬ ይሙት ” ብለው እንደሚምሉ የሚነገርላቸው ሰው ናቸው ። እናም በአንድ ወቅት ፡ አብዛኛዎቹ የደርግ ጄኔራሎች ህወሃት ደርግን አላሸነፈም ይላሉና እርሶስ ይህን በተመለከተ ምን ይላሉ በማለት ቀርቦላቸው ለነበረው ጥያቄ እንዲህ በማለት ነበር የመለሱት ።

” ሰራዊቱን የሚመራው ፖለቲካው ነው ። አንደኛ በዛን ሰአት መፈንቅለ መንግስት መካሄድ አልነበረበትም ። በመፈንቅለ መንግስቱ እነ ጄኔራል ደምሴ ሞቱ ፡ እነ ጄኔራል ታደሰ ሞቱ የመረጃ ክፍል ሃላፊው ጄኔራል ከበደ ሞቱ ብዙ ሰው አጥተናል እኛ በሙሉ ታሰርን ፡ የሰሜን እዝ የመረጃ ሰወች በሙሉ የሉም በዚህም ምክንያት ቤቱ ክፍት ነው ።

ሁለተኛ ውስጣችን የተሰገሰጉ ሰወች አሉ ። ለምሳሌ አሜሪካኖች በፖለቲካው ምክንያት ጠላቶቻችን ናቸው የአውሮፓ ህብረትን ውሰድ ፡ አረብ ሃገራትን ውስድ ይሄ ሁሉ ተዳምሮ ህዝቡም በመሰልቸት ላይ ስለነበረ ፖለቲካው እንጂ ህወሃት ደርግን በጭራሽ አላሸነፈም ። ሻእቢያን እየገረፍነው አይደል እንዴ ናቅፋ ያስገባነው ? ማነው ይህን ያደረገ እኛው ነንኮ ወያኔን እዛ ደደቢት ድረስ ሄጄ መትቻት ነው የመጣሁት ። ኦፊሻሊ እኛ ነን አሸነፍን ይላሉ ደርግ ጠላቱ ብዙ በመሆኑ እንጂ በጭራሽ ህወሃት አላሸነፈችውም በጭራሽ አላሸነፈችውም ። እኛ እርስ በርስ እንተዋወቃለን ።

* ታሪክን የኋሊት *
የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም
(የካራ ማራ ድል _ 42ኛ ዓመት)

” ማን ይፈራል ሞት
ማን ይፈራል
ለእናት ሃገር ሲባል!”

Image may contain: 1 personየሶማሊያው መሪ ዚያድ ባሬ ” ታላቋ ሶማሊያ”ን እመሰርታለሁ በሚል ቅዠት ኢትዮጵያን በመውረሩ ህዝቡ ለሀገሩ ዳር ድንበር ዘብ እንዲቆም ጓድ ሊቀመንበር መንግሥቱ ኃ/ማርያም ሚያዝያ 4 ቀን 1969 ዓ.ም በቴሌቭዥን መስኮት ቀርበው ጥሪ አስተላለፉ።

“… ታፍራና ተከብራ የኖረችው ኢትዮጵያ ተደፍራለች። … ለብዙ ሺህ አመታት አስከብሮን የኖረው አኩሪ ታሪካችን በዚህ አብዮታዊ አዲስ ትውልድ ጊዜ መጉደፍ የለበትም። አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያዊት! የኢትዮጵያ ሕዝብ! ለክብርህንና ነፃነትህን ለመድፈር አገርህን ለመቁረስ የተጀመረው ጣልቃ ገብነትና ወረራ ከመለዮ ለባሹ ጋር ተሰልፈህ ለመደምሰስ የምትዘጋጅበት ጊዜ አሁን ነው። ተነስ! ታጠቅ! እናሸንፋለን!”

ከዚህ ጥሪ በኋላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዳር እስከ ዳር ገንፍሎ ተነስቶ በ3 ወር ግዜ ውስጥ ታጠቅ ተብሎ በተሰየመው ማሰልጠኛ ቦታ ሰልጥኖ ከኩባ፣ በሶቪየት ሕብረት እና ምስራቅ ጀርመን አንዲሁም የመን ጋር በጋራ በመሆን ትልቁን የካራ ማራ ድል የተጎናፀፉ።

በጦርነቱ በኢትዮጵያ ወገን 18.200 ኢትዮጵያውን ሞተዋል፤ 29.100 ቆስለው 7 የተማረኩ ሲሆን 100 የመናዉያን እና 163 የኩባ ተወላጆች ለኢትዮጵያ ህይወታቸውን ሰጥተዋል። በሶማሊያ በኩል ደግሞ 15.900 ሞተዋል፣ 26.000 ቆስለው 1785 ተማርከዋል።

ከካራማራ ድል በኋላ ኢትዮጵያን ወርሬ ታላቋን ሶማሊያ እመሰርታለሁ የሚለው የዚያድ ባሬ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ሶማሊያን እስከ ማፍረስ ደረጃ አደረሳት። ኢትዮጵያን ነክቶ የቀጠለ አንድም ትዕቢት የለም። ታሪክ ምስክር ነው!

እናም በዛሬው ቀን የተፈፀመው ቀንዲል ታሪክ ይህን ነው። የካራማራ ድል!

በብዙ ጦርነቶቸ መሓል፣ ለዚያውም በሀገር ወስጥ ውጊያ ላይ የነበሩት ትህነግ ፣ ኢህአፓ ጭምር ሶማሊያ አግዞ ደርግን ይወጋበት በነበረት ግዜ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውን ህይወታቸውን ገብረው ዳር ድንበራቸውን በደም መስዋዕትነት ያስከበሩበት ቀን ነው!

ዘላለማዊ ክብር ለኢትዮጵያ ዳር ድንበር መከበር ለተዋደቁት ሁሉ!

ማጣቀሻ መፅሐፍት ፤
_ ትግላቸን ቅፅ ፩ __ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም
_ እኛና አብዮቱ ― ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ
_ አብዮቱና ትዝታዬ _ ሎ/ኮሎኔል ፍሥሐ ደስታ