በደብረዘይት ለተሰበሰቡ የብልጽግና ፓርቲ አባላት የሚከፈል 2 ሚሊዮን ብር አበል ከአቶ ታዬ ደንድዓ መኪና ውስጥ መዘረፉ ተሰማ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


BBC Amharic የብልጽግና ፓርቲ አመራር የሆኑት አቶ ታዬ ደንደአ በቢሸፍቱ ከተማ ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው ብርና ሌሎች ንብረቶች ዝርፊያ እንደተፈጸመባቸው ለቢቢሲ ተናገሩ።

አቶ ታዬ ዘረፋው ያጋጠማቸው ለሥራ ጉዳይ ወደ ቢሾፍቱ በሄዱበት ወቅት መሆኑንና በዚህም ይጓዙበት ከነበረው መኪና ውስጥ ሁለት ሚሊዮን ብር እና ሌሎች ንብረቶች እንደተወሰደባቸው ገልጸዋል።

ዝርፊያው የተፈፀመበት ሁኔታም ሲያስረዱም፤ ቢሾፍቱ ከተማ ውስጥ ቢን ኢንተርናሽናል በተባለ ሆቴል ምሳ ለመመገብ መኪናቸውን አቁመው በገቡበት ጊዜ “የመኪናቸው በር በማስተር ቁልፍ ተከፍቶ” የተጠቀሰው ገንዘብና የተለያዩ ንብረቶች እንደተዘረፈባቸው ተናግረዋል።

አቶ ታዬ ደንደኣ

ይህ ከፍተኛ መጠን ያለውን ገንዘብ በመኪናቸው ይዘው የነበረው በቢሾፍቱ ከተማ ስልጠና እየተከታተሉ ለነበሩ ለሰልጣኞች የሚከፈል አበል እንደነበር ጨምረው አስረድተዋል።

ከገንዘቡ በተጨማሪ ላብቶፕ ኮምፒውተር እና ሁለት የሥራና የግል ጉዳዮችን የሚጽፉባቸው ማስታወሻ ደብተሮች እንደተሰረቁባቸው ተናግረዋል።

ጨምረውም ስርቆቱ ከተፈፀመ በኋላ “የታዬ ማስታወሻ ደብተር እጄ ገብቷል” ብሎ የፌስቡክ ገፁ ላይ የጻፈ ግለሰብ መኖሩንና ጉዳዩን ወደ ሕግ መውሰዳቸውንም ያስረዳሉ።

የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ ስለጉዳዩ ተጠይቆ ምርመራ እየተካሄደ ስለሆነ ተጣርቶ ሲያልቅ ይፋ እንደሚደረግ የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ደረጀ ሙለታ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የአቶ ታዬ ደንደአ የማስታወሻ ደብተር መሰረቁን ፌስቡክ ገፁ ላይ ጻፈ ያሉት ግለሰብ በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ በማህበራዊ ሚዲያዎች ሃሳብ በመስጠት የሚታወቀው ደረጀ ቤጊ የተባለ ግለሰብ ነው።

በጉዳዩ ላይ ቢቢሲ ያነጋገራቸው አቶ ደረጀ “እንደማንኛውም ጊዜ በፌስቡክ የመልዕክት ሳጥኔ እንደተላከልኝ አስታውቄ ነው ማስታወሻዎቹ መሰረቃቸውን የፃፍኩት” ብለዋል።

“በውስጥ መስመር ነው የተላከልኝ፤ የለጠፍኩትም [ኢንቦክስ] ብዬ ነው። ታዬ መዘረፉንም ሆነ ስለ እርሱ ምንም የማውቅው ነገር የለኝም” ብለዋል።

አቶ ታዩ ደንደአ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ሲሆኑ በመገናኛ ብዙህን እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያዎች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የፓርቲያቸውንና የራሳቸውን አቋም በመግለጽ ይታወቃሉ።