በመጭው ሐሙስ በተለያየ አቋማቸው የሚታወቁት ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጣቸው ፖለቲከኞች ይወያያሉ፣ ይከራከራሉ የተባለው ፕሮግራም ተሰረዘ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው በመጭው ሐሙስ በተለያየ አቋማቸው የሚታወቁት ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጣቸው ፖለቲከኞች ይወያያሉ፣ ይከራከራሉ የተባለው ፕሮግራም በተጋባዥ ተናጋሪዎች እምቢተኝነት ተሰረዘ ::

በኢትዮጵያ ፓለቲካ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጣቸውና በተለያየ አቋማቸው የሚታወቁት ፖለቲከኞች በአንድ መድረክ ሊመጡ ነው የተባለው ፕሮግራም ተሰረዘ።ፕሮግራሙን ያዘጋጀው ተቋም ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉን ገልጿል።

Our highly anticipated dialogue forum Democratic Transition in Ethiopia on 13 Feb. 2020 is indefinitely postponed due to unexpected commitments of some of the speakers who won’t be available for the event and to make it as inclusive as possible. The new date will be announced.

“ዲሞክራሲያዊ ሽግግር በኢትዮጵያ፡ ተስፋና መሰናክሎች” በሚል ርዕስም ጃዋር መሃመድ (ኦፌኮ)፣ ደሳለኝ ጫኔ (አብን)፣ ጌታቸው ረዳ (ህወሃት)፣ ልደቱ አያሌው (ኢዴፓ)ና አንዱአለም አራጌ (ኢዜማ) ና ሌሎች ፖለቲከኞች ይወያያሉ፣ ይከራከራሉ የተባለው ፕሮግራም ተሰረዘ።በተቻለ መጠን ሁሉን አቀፍ የተናጋሪዎችና ተወያይ ተከራካሪዎች መድረክ ለማዘጋጀት ይቻል ዘንድ በቅርቡ አዲሱ ቀን ይፋ ይደረጋል ፡፡

የውይይት መድረኩ የተዘጋጀው በኢትዮጵያ ስትራቴጂክ ጥናት ተቋም አማካኝነት ሲሆን በባለፉት ሁለት አመታት ኢትዮጵያ ያደረገችውን ዲሞክራሲያዊ ሽግግር፤ሃገሪቷን ቀውስ ውስጥ የከተተው መፈናቀል፣ ግድያና ግጭት፤ ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም መጪው ምርጫንም በተመለከተ ያላቸውን ሃሳብ ያጋራሉ። ውይይት ሐሙስ የካቲት 5፣ 2012 ዓ.ም ከጥዋቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ በስካይት ላይት ሆቴል የሚካሄድ ይሆናል።ተብሎ የነበረ ቢሆንም ፕሮግራሙን ያዘጋጀው ተቋም ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉን ገልጿል።

Source – @ISAffairs_

Image