" /> የሕዳሴ ግድብ የዋሽንግተን ተደራዳሪ ቡድኖች ስምምነት ላይ ሊያደርስ የሚችል ሰነድ ለማዘጋጀት አልቻሉም ተባለ | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

የሕዳሴ ግድብ የዋሽንግተን ተደራዳሪ ቡድኖች ስምምነት ላይ ሊያደርስ የሚችል ሰነድ ለማዘጋጀት አልቻሉም ተባለ

ዋሽንግተን ዲሲ በፌብሩዋሪ 12/20 ቀጠሮ መሰረት የውሃ: መስኖና ኢነርጂ ሚ/ር ዶ/ር ስለሺ በቀለ ዋሽንግተን ዲሲ ገብተዋል:: በዕለቱም ሳምንቱን ሙሉ ከግብጽና ሱዳን ጋር የተደረገውን የህግ ማዕቀፍ ድርድር ውጤት ከኢትዮጵያ ሉዑካን ጋር ገምግመዋል::

ቡድኑ በብዙ ጉዳዮች ላይ የመከረ ቢሆንም ስምምነት ላይ ሊያደርስ የሚችል ሰነድ ማዘጋጀት አለመቻሉ ታይቷል:: ኢትዮጵያ በፍትሃዊና ምክንያታዊ ተጠቃሚነት የምታምን ሲሆን: በአባይ የመጠቀም መብቷን አሳልፎ የሚሰጥ ምንም ዓይነት ስምምነት አትፈጽምም!

አምባሳደር ፍፁም አረጋ


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV