የእነ አቶ በረከት ስምዖንን የመከላከያ ምስክሮች ቃል የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማድመጥ ጀመረ


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።

ፍርድ ቤቱ የእነ አቶ በረከት ስምዖንን የመከላከያ ምስክሮች ቃል ማድመጥ ጀመረ

(ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የእነ አቶ በረከት ስምዖንን የመከላከያ ምስክሮች ቃል ማድመጥ ጀምሯል።

ፍርድ ቤቱ ታህሳስ 30 ቀን 2012 በዋለው ችሎት ዓቃቤ ህግ አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ ለተመሰረተባቸው ክስ ያቀረቧቸውን የመከላከያ ቃል ምስክሮች ለማዳመጥና የሰነድ ማስረጃዎች ለመመልከት ለጥር 4 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወቃል።

በወቅቱ ፍርድ ቤቱ በዋለው ችሎትም የተከሳሽ ጠበቆች በ4ቱ ክሶች አሉን ያሏቸውን የሰነድና 11 የቃል መከላከያ ምስክሮች አቅርበዋል።

ጥር 4 ቀን 2012 ዓ.ም በተሰየመው ችሎት ደግሞ የተከሳሽ የመከላከያ ምስክሮች የምስክር ቃል ከማሠማታቸው በፊት ተከሣሳሾች የተከሰሱበትን ቃል በማቅረባቸው ምክንያት ፍርድ ቤቱ የምስክሮቹን ቃል ለማዳመጥ በድጋሜ ለጥር 5 ቀን 2012ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤትም በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎትም የተከሳሽ ጠበቆች አሉን ካሏቸው 11 የቃል ምስክሮች አራቱን ያቀረቡ ሲሆን፥ ሶስቱ ግን ሊቀርቡላቸው እንዳልቻሉ አስረድተዋል።

በዚህ መሰረትም ፍርድ ቤቱ የተከሳሽ ጠበቆች ካቀረቧቸው አራት የቃል ምስክሮች ውስጥ የአንደኛው ቃል አድምጧል።

የቃል ምስክሩ በደቨንቱስ ስማርት ሜትር የውሃና የመብራት ብክነት አቅረቦት መቆጣጠሪያ ስራ መጀምር አስመልክቶ የምስክርነት ቃሉን አሰምታል።

የምስክርነት ቃሉን ያሰማው የመከላከያ ምስክር ፕሮጀክቱ ወደ ማምራት ስራ መግባተን ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።

ዓቃቤ ህግ በበኩሉ ጀመረ የተባለው የደቨንቱስ የስማርት ሜትር በውሃና ኤሌክትሪክ መቆጣጠሪያ የጥረት ቦርድ ያልወሰነበት እና የጥራት ማረጋገጫ የለውም በማለት ተከራክራል።

የግራ ቀኙን ክርክር የተመለከተው ፍርድ ቤትም ቀጣይ የተከሳሽ ጠበቃ መስቀለኛ ጥያቄን ለመስማት ከሰዓት በኋላ ቀጥሯል።

የቀሪዎቹ ምስክሮች ቃልም ከሰዓት በኋላ መደመጥ ሚቀጥል መሆኑ ተመላክቷል።