መንግስት ከታገቱበት ተለቀዋል ያላቸውን ተማሪዎች በሚዲያ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርጋቸው የአብን ሊቀመንበር ጠየቁ


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ትላንት ምሽት 4 ሰዓት ወደ ታገቱ ተማሪዎች ወላጆች እንደደወሉና ወላጆችም ስለልጆቻቸው መለቀቅ መረጃ እንደሌላቸው እንደገለፁላቸው በትዊተር ገፃቸው ገልፀዋል!

ሊቀመንበሩ ትላንት ምሽት አቶ ንጉሱ ጥላሁን በመንግስት ድርድር ተለቀዋል ያሏቸው ተማሪዎችን ዛሬ በሚዲያዎች እንዲያቀርቧቸው ጠይቀዋል። ዶ/ር ደሳለኝ የታገቱ ተማሪዎች ስምና ፎቶዓቸው አለንም ብለዋል። Via Tikvah-Eth